IMG_6617

የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን እንደፈረሰ ተሰማ

In News by Konso People2 Comments

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አከባቢ ከፈደራል መንግስት ከፍተኛ አመራር በአርባምንጭ  በተደረገ ስብሰባ ላይ የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን እንዲበተንና ወረዳዎቹ ወዴየቀደሞ መዋቅራቸው (ልዩ ወረዳ) እንድመለሱ ተደርጓል የሚል ጭምጭምታ በከፍተኛ ሁነታ እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

ይህ ዜና ለኮንሶ ህዝብ ከፍተኛ ድል መሆኑን ጭምር በስፍራው የሚገኙ ነዋርዎች ገልፀዋል፡፡

እሰከአሁን ድረስ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ይህ ዜና ለህዝቡ እፎይታን እንደፈጠረ ከስፈራው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ማሳሰቢያ

በ October 7, 2016 በአቶ ገመቹ ገሸርቶ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ድብደባ ህይወቱ እንዳለፈች ዘግበን ነበር፡፡ እንዲሁም ያለውን ሁኔታ ተከታትለን በስፋት መረጃውን ወደ እናንተ  አናደርሳልን! ብለን ነበር ፡፡ በጊዜው በአቶ ገመቹ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ድብደባ የተነሳ እራሱን ስቶ ስለነበረ በድንጋጠ ህይወቱ እንዳለፈ መረጃ ስለደረሰን ነበር አሁን ባጣራነው መሠረት ህይወቱ እነዳላለፈችና በከፍተኛ ሰቃይ ውስጥ እንዳለ ነው፡፡

Comments

 1. አባሂሩት ባጫ

  ላለፉት አንድ ዓመት ተኩል የኮንሶ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄን ለማኮላሸት የክልሉ ቡድን ብዙ ዘግናኝ ኢሰብአዊ ዘዴዎችን ተጠቅሟል አሁን ደግሞ ከበፊቱ ይልቅ አጠናክረው በሀይል እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦችን በሀገርቱ ሀብት/ብር እየገዙ ግጭቶችን እየቀሰቀሱ ይገኛሉ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ጋነኖቹ የባለሥልጣናት ቡድን አካሄድ ለዘጎቻችን እልቂት ቢሆንም ለእነሱ ግን በሚፈሰው የኮንሶ ደም ጮበ እየረገጡ ይገኛሉ፡፡ የሕዝቡ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ በእጅጉ አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ችግራችንን ከክልል እስከ ፌደራል መንግስት ድረስ ሪፖርት ቢደረግም “መጽሐፍ ዝም ቄሱም ዝም” እንደሚባለው ከአፃዎቹ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ እልቂት በሕዝባችን ላይ ስፈፀም ሀይ የሚል አካል ጠፍቷል፡፡በአሁኑ ወቅት ዘግናኝ ድርጊቶች በኮንሶ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የባለሥልጣናት ቡድን ዜደ በእጅጉ የረቀቀ ነው፡፡ ይኸውም የኮንሶ ዋና ከተማ ካራት ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ እንግዶች ማረፊያ እንደ መሆኑ መጠን በከተማው ላይ የጅምላ ሕዝብ ቅጥቀጣና ሰዶ ማሳደድ ሳይሆን የግለሰቦችን ቤት ብቻ ለሊት እየሰበሩ ባለቤቶችን በመያዝ ንብረቶች ይዘርፋሉ፡፡ በከተማው ያሉ ወፍጮ ቤቶችና የውሃ አገልግሎቶች አልታሸጉም፡፡ የግል ክልንኮችና ፋርማሲዎች ግን ታሽገዋል እየታሸጉም ይገኛሉ፡፡ ላለፉት በርካታ ጊዜያቶች በከተማ ያለውን ገበያ ሥፍራ ስበጠብጡ ቆይተው አሁን ግን ስልትን በመቀየስ ለገበያው ጥንቃቄ እያደረጉ ግለሰቦችን ከውስጥ ያሳድዳሉ፡፡ በገጠርቱ ስደት ላይ ያሉ ማንኛውም ነዋሪዎች ወደ ከተማ ለገበያ ስመጣ ግብይቱን ያካሄዳል ግን በቀበሌው ከጠቅላላ ነዋሪዎች ጋር የጅምላ ስደትና እስራት ቀማሽ ይሆናል፡፡ይህንን የሚጠቀሙት ግን ባለሥልጣናቶቹ ለሕዝብ አዝነው ሳይሆን የእነሱ ሥዕል እንዳይበላሽ ጥንቃቄ በማድረግ ነው፡፡አርሶአደሮችን ለማንበርከክ በገጠርቱ የሚፈፀመው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ድርጊቱም ልብ የሚነካ ጉዳይ ነው፡፡ሁላችን እንደሚናውቀው ፖልትከኞቹ ዓላማቸውን ለማሳከት አፀያፊ ድርጊት እየፈፀሙ ለሚዲያዎች ግን እውነታውን ይክዳሉ፡፡ እስቲ በሁሉም ቀበሌዎች የሚፈፀሙ ከደርጋዊ አገዛዝ የበለጠ ተግባራትን ከብዙ ጥቂቶቹ እነሆ፡-

  1/ ወፍጮ ቤቶች እና ውሃ ተቋማት ከታሸጉ ሳምንታት አልፈዋል፡፡የመኪና ስምርት ወደ ቀበሌዎች እንዳይመደብ አግደዋል፡፡ከሁሉም የሚገርመው አርሶአደሮቻችን የሰዓታት መንገድ በእግር ተጉዘው በካራት ከተማ የወፍጮ እና የውሃ አገልግሎት እንዳያገኙ ልዮ ሀይሎቹ በየመንገድ ጥበቃ እያደረጉ ወደ ከተማ እህልና የውሃ ጀርካኖችን እንደ ኮንትሮባንድ መያዝ ጀምረዋል፡፡ ድንገት አምልጦ አገልግሎትን አግኝቶ የሚመለስ ሰው ከተገኘ ንብረቱ ይወረስና ይታሰራል፡፡
  2/ ሁሉም የመንግሥት ጤና ተቋት ካቋረጡ ዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ሕዝቡ ግን በየገጠር ያሉ የግል ተቋማትን ስጠቀሙ ነበር፡፡ ይሁንና ሕዝቡን ለማንበርከክ በገጠርቱ ያሉትን ሁሉም የግል ጤና ተቋማት አሽገዋል፡፡ የተሽከርካሪ አቅርቦት የተቋረጠ በመሆኑ ሕዝቡ በሽተኛን በቃረዛ ተሸክመው በአማካይ ከሶስት ሰዓት እስከ አስር ሰዓት በእግር ተጉዘው በካራት ከተማ ሕክምና እያገኙ ነበር፡፡ ይሁንና ከትላንት 26/3/2009 ዓ.ም ጀምሮ ከርቀት መጥተው በከተማው የሕክምና አገልግሎት ሊያገኙ ወረፋ እየጠበቁ የነበሩትን ታካሚዎችን አባሪረው ክልንኮችና ፋርማሲዎችን ማሸግ ጀምረዋል፡፡
  3/ የመንግሥት ሠራዊት ሁሉም ቀበሌዎችን እየከበቡ ግለሰብ ሳይለይ በጅምላ ከልጅ እስከ አዛውንት ድረስ በዱላ እና በሰደፍ እየቀጠቀጡ ወደ ማሰቃያ ሥፍራዎች ይወሰዳሉ፡፡ ይህ ድርጊት የአንድ ቀን ብቻ ቢሆን መልካም ነበር ግን ሠራዊት እና ኪራይ ሰብሳቢ አመራሮች በጋራ ተቀናጅተው በሁሉም ቀበሌዎች ስምሪት ወስደው እዚያ መኖር ከጀምሩ ብዙ ወራቶች ሆኗል፡፡ ከዚህ የተነሳ ጠቅላላ የየቀበሌዎቹ ነዋሪዎች መኖሪያቸው ለቅቀው ኑሮ ጫካ አድርገዋል፡፡ በየጫካ ሕክምና በማጣት÷በረሃብና ጥም÷በወልድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቤት ይቁጠረው፡፡ በዚህ ብቻ ብያበቃ ጥሩ ነበር ነገር ግን የክልሉ ቡድን በገንዘብ በገዛቸው ጠቋሚዎች አማካይነት ሠራዊቱን አስከትለው እስከ ጫካ በመምጣት የሚገድሉትን እየገደሉ የሚፈልጉትን ወደ ፊት ላይጠቅም በዘግናኝ አካላዊ ድብደባ ወደ ማጎሪያ ቤቶች ይወስዳሉ፡፡ እዚያም ሕክምና አይታሰብም፡፡
  4/ በየገጠርቱ ያሉ ሁሉም ት/ቤቶች እና ጤና ተቋማት ተዘግተው እነዚያ መሥሪያቤቶች የወታደር ካምፕ ሆነዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው የፖልትከኞቹ ድራማ ግን ት/ቤቶች አገለግሎት እየሰጠ መሆኑን ለማስመሰል በውስን ት/ቤቶች ባንድራ ብቻ እያውለበለቡ ይገኛሉ፡፡ እውነታው ግን በካራት ሙሉ 1ኛ ደረጃና ካራት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ ሃምሳ የማይሞሉ የኮንሶ ዘጎች ያልሆኑ ተማሪዎች ቢመዘገቡም እነሱ ራሳቸው በአግባቡ እየተማሩ አይደሉም፡፡
  5/ ዜጎች በስደት ላይ እያሉ ብዙ ሴቶች የኮንሶ ባህል በእጅጉ የሚፀየፈውን አስገዲዶ መድፈር በሠራዊቱ አማካይነት ይፈፀማል፡፡
  6/ የጅምላ እስራትም በሁሉም ቀበሌዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ፆታና ግለሰቦችን ሳይለይ ከሕፃናት እስከ አዛውንት ድረስ ተቀጥቅጠው ይታሰራሉ፡፡ ለአብነት ብቻ ትላንት 26/3/2009 ዓ.ም ኮልሜ አገልግሎት የተከሰተውን አንዱን ሰብዓዊነት የጎደለውን ድርጊት ላስታውሳችሁ-የአመራሩ ምስት ከወለደች አራት ቀን ቢሞላትም ሠራዊቱ ባነሳው ሽብር የተነሳ ቤቷን ለቅቃ በአከባቢው ባለ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ከጨቅላ ሕፃኗ ጋር ተጠቅልላ ባለችበት በድንገት ሠራዊቱ ዓይን ሥር ገብታ እየተቀጠቀጠች”ባልሽ የት ነው ያለው” ስትባል “የት እንዳለ አላውቅም” ብላ ስትመልስ “ባልሽ ሕፃኑን ያምጣ” ብለው እሷን ብቻ ወደ ኃላ አስረው ወደ ካራት ከተማ ለእስር አመጧት፡፡በየቦታ የታሰሩ እስረኞች ከ 3ሺህ በላይ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል
  7/ በመጀመሪያዎቹ አከባቢ የኮንሶ ወረዳ አንዱ ቀበሌ የሆነውን አባሮባ ሕዝብን ለሁለት ከፍለው ሰባት መንደሮችን በመያዝ ነዋሪዎች እና ሠራዊቱ በጋራ ሆነው ሁለት የቀበሌን መንደሮች ለመዋጋት ተነስተው የአንዱን መንደር “አማራይታ” ነዋሪዎችን ተዋግተው ብዙ ሰዎችን ከገደሉ በኃላ ቤቶቹን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው ወደ አመድነት ቀይረዋል፡፡ ቅርብ ጊዜ ደግሞ ቀሪውን መንደር”ኮርማሌ” ነዋሪዎችን ተዋግተው የተወሰኑ ቤቶችን አቃጥለዋል፡፡ በዚህ ብቻ ሳያበቃ በሠራዊቱ ሥር ያሉት መንደሮች ከልዮ ሀይሎች ጋር በመተባበር ለአባሮባ አጎራባች ቀበሌዎችን(ጌራ÷ካሻሌ÷መጨቀ) በከባድ መሣሪያ እየተዋጉ አያለ ሰዎችን በመግደል ንብረቶችን አቃጥለዋል እስከ ትላንት ድረስ ትንኮሳውን አልተውም፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የባለሥልጣናት ቡድን እነኚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ሌሎችም ያልተጠቀሱ በርካታ ወንጀሎች እየሠሩ ጥፋቱን ወደ ሌላ አካል “ባህላዊ ቡድን” እያሉ ማባበያ ይሰጣሉ፡፡ “ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ” ይሉታል፡፡
  ይህ በዚህ እንዳለ ኮንሶ በአሁኑ ወቅት የጥንት ዳርፉር ትመስላለች፡፡በሠራዊቱ ከሚገደለው ውጪ ሰዉ በየቦታው ሞቶ ይቀራል በማን እንደተገደለም አይታወቅም፡፡
  የደርግ መንግስት የሀገርቷን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ አንድን ግለሰብ ብቻ አሳምኖ ወይም አባሮ ይይዛል እንጂ እንደዚህ ዓይነት አፀያፊ በደሎች በጠቅላላ በኮንሶ ላይ ፈጽሞ አያውቅም፡፡ ከአባቶቻችን በታርክ እንደምንሰማው ከደርግ በፊትም የነበሩ መንግሥታት የኮንሶ ሕዝብን እንደዚህ ፊዳ አሳይቶ አያውቅም፡፡ ወደ ፊትም ማንኛውም ማካካሻ ሥራ ለሕዝቡ ቢደረግም ምሁሩም ሆነ አርሶአደሮቻችን የደረሰበትን በደል ፈጽሞ አይረሳውም፡፡ ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ዕድሜ ከሰጠን አብረን የሚናየው ጉዳይ ነው፡፡
  በዚህ ሁሉ ግን ሕዝቡ ትላንት ሕገመንግሥታዊ ጥያቄውን አጥብቆ እንደያዘ ሁሉ ነገም ቢሆን እስከ መጨረሻ ኢሰብዓዊ በደሎችን በፀጥታና በሰላማዊ መንገድ እየተቋቋመ ሕገመንግሥቱን በመጠበቅ ለመብቱ በጽናት ይቆማል፡፡
  ነፃነትና ፍትህ ለጭቁኑ ኮንሶ ሕዝብ !!
  ለአፍታም ቢሆን ጥያቄያችን አይቋረጥም!!
  የኮንሶ ሕዝብ ፍትህ ፈላጊ እንጂ አሸባሪ እና ግንቦት 7 አይደለም!!

 2. abahiru

  Thanks !!
  we konso people will never be continue under the hael of segen suroundin peoples zone;
  we are not fewer nations, we will countinue ouer struggle!!
  ማዲካታ ቀረዬ ኦኦፐ ኩራሾ ለሚታ ክዶ !!!!!!!!

Leave a Comment