IMG_6617

የኮንሶ ማህበራዊ ድህሬ-ገጽ konsopeople.com በGoogle ከፍተኛ ደረጃ አገኘ፡፡

In Standard by Konso People2 Comments

የህዝብ ድምፅ የሆነው የኮንሶ ህዝብ ማህበራዊ ድህሬ-ገጽ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሱ ያሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ በደሎች በፍጥነት ወደ ህብረተሰቡ በቀጥታ እንድደርስ በሚል አላማ የተሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጎግል የፍለጋ ድህረ-ገፅ የመጀመርያ ገፅ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመታየት በቅቷል፡፡ ይህ ማለት፡ – ማነኛውም ሰው ከየትም ቦታ ሆኖ የጎግል ገጽ ላይ Konso  ወይም Konso People ብሎ ብጽፍ በቀጥታ የመጀመርያው ገፅ ላይ የድህሬ-ገጹን አድራሻ ያገኘዋል:: ይሄም የኮንሶ ህዝብን ድምፅ ተደራሽነት በእጅጉ ያልቀዋል ተብሎ ይጠበዋል፡፡

111

ሁሉም የኮንሶ ተወላጅ በአሁኑ ወቅት በህዝቡ ለይ እየደረሰ ያለውን ጫናና በደልን እንዲያወግዘውና በተቻለው መጠን መረጃዎችን በድህሬ-ገጹ  ላይ ሼር በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ በአክብሮት ተጋብዟል፡፡

ድል ለታሪክ ሠሪው ህዝብ!

Comments

 1. አባሂሩት ባጫ

  በኮንሶ ህዝብ አሁንም በደቡብ ክልል አመራሮች እየተሰቃየ ይገኛል።
  በኮንሶ ምን እየሆነ ነው ያለው?
  ላለፉት አንድ ዓመት ተኩል የኮንሶ ሕገመንግሥታዊ ጥያቄን ለማኮላሸት የክልሉ ቡድን ብዙ ዘግናኝ ኢሰብአዊ ዘዴዎችን ተጠቅሟል አሁን ደግሞ ከበፊቱ ይልቅ አጠናክረው በሀይል እየተጠቀሙ ይገኛሉ፡፡ በጣት የሚቆጠሩ ግለሰቦችን በሀገርቱ ሀብት/ብር እየገዙ ግጭቶችን እየቀሰቀሱ ይገኛሉ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ጋነኖቹ የባለሥልጣናት ቡድን አካሄድ ለዘጎቻችን እልቂት ቢሆንም ለእነሱ ግን በሚፈሰው የኮንሶ ደም ጮበ እየረገጡ ይገኛሉ፡፡ የሕዝቡ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ጉዳይ በእጅጉ አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ችግራችንን ከክልል እስከ ፌደራል መንግስት ድረስ ሪፖርት ቢደረግም “መጽሐፍ ዝም ቄሱም ዝም” እንደሚባለው ከአፃዎቹ ጀምሮ ታይቶ የማይታወቅ እልቂት በሕዝባችን ላይ ስፈፀም ሀይ የሚል አካል ጠፍቷል፡፡በአሁኑ ወቅት ዘግናኝ ድርጊቶች በኮንሶ ወረዳ በሁሉም ቀበሌዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ የባለሥልጣናት ቡድን ዜደ በእጅጉ የረቀቀ ነው፡፡ ይኸውም የኮንሶ ዋና ከተማ ካራት ከተለያዩ ሀገራት የሚመጡ እንግዶች ማረፊያ እንደ መሆኑ መጠን በከተማው ላይ የጅምላ ሕዝብ ቅጥቀጣና ሰዶ ማሳደድ ሳይሆን የግለሰቦችን ቤት ብቻ ለሊት እየሰበሩ ባለቤቶችን በመያዝ ንብረቶች ይዘርፋሉ፡፡ በከተማው ያሉ ወፍጮ ቤቶችና የውሃ አገልግሎቶች አልታሸጉም፡፡ የግል ክልንኮችና ፋርማሲዎች ግን ታሽገዋል እየታሸጉም ይገኛሉ፡፡ ላለፉት በርካታ ጊዜያቶች በከተማ ያለውን ገበያ ሥፍራ ስበጠብጡ ቆይተው አሁን ግን ስልትን በመቀየስ ለገበያው ጥንቃቄ እያደረጉ ግለሰቦችን ከውስጥ ያሳድዳሉ፡፡ በገጠርቱ ስደት ላይ ያሉ ማንኛውም ነዋሪዎች ወደ ከተማ ለገበያ ስመጣ ግብይቱን ያካሄዳል ግን በቀበሌው ከጠቅላላ ነዋሪዎች ጋር የጅምላ ስደትና እስራት ቀማሽ ይሆናል፡፡ይህንን የሚጠቀሙት ግን ባለሥልጣናቶቹ ለሕዝብ አዝነው ሳይሆን የእነሱ ሥዕል እንዳይበላሽ ጥንቃቄ በማድረግ ነው፡፡አርሶአደሮችን ለማንበርከክ በገጠርቱ የሚፈፀመው ግን ከዚህ የተለየ ነው፡፡ ድርጊቱም ልብ የሚነካ ጉዳይ ነው፡፡ሁላችን እንደሚናውቀው ፖልትከኞቹ ዓላማቸውን ለማሳከት አፀያፊ ድርጊት እየፈፀሙ ለሚዲያዎች ግን እውነታውን ይክዳሉ፡፡ እስቲ በሁሉም ቀበሌዎች የሚፈፀሙ ከደርጋዊ አገዛዝ የበለጠ ተግባራትን ከብዙ ጥቂቶቹ እነሆ፡-
  1/ ወፍጮ ቤቶች እና ውሃ ተቋማት ከታሸጉ ሳምንታት አልፈዋል፡፡የመኪና ስምርት ወደ ቀበሌዎች እንዳይመደብ አግደዋል፡፡ከሁሉም የሚገርመው አርሶአደሮቻችን የሰዓታት መንገድ በእግር ተጉዘው በካራት ከተማ የወፍጮ እና የውሃ አገልግሎት እንዳያገኙ ልዮ ሀይሎቹ በየመንገድ ጥበቃ እያደረጉ ወደ ከተማ እህልና የውሃ ጀርካኖችን እንደ ኮንትሮባንድ መያዝ ጀምረዋል፡፡ ድንገት አምልጦ አገልግሎትን አግኝቶ የሚመለስ ሰው ከተገኘ ንብረቱ ይወረስና ይታሰራል፡፡
  2/ ሁሉም የመንግሥት ጤና ተቋት ካቋረጡ ዓመት በላይ አስቆጥሯል፡፡ ሕዝቡ ግን በየገጠር ያሉ የግል ተቋማትን ስጠቀሙ ነበር፡፡ ይሁንና ሕዝቡን ለማንበርከክ በገጠርቱ ያሉትን ሁሉም የግል ጤና ተቋማት አሽገዋል፡፡ የተሽከርካሪ አቅርቦት የተቋረጠ በመሆኑ ሕዝቡ በሽተኛን በቃረዛ ተሸክመው በአማካይ ከሶስት ሰዓት እስከ አስር ሰዓት በእግር ተጉዘው በካራት ከተማ ሕክምና እያገኙ ነበር፡፡ ይሁንና ከትላንት 26/3/2009 ዓ.ም ጀምሮ ከርቀት መጥተው በከተማው የሕክምና አገልግሎት ሊያገኙ ወረፋ እየጠበቁ የነበሩትን ታካሚዎችን አባሪረው ክልንኮችና ፋርማሲዎችን ማሸግ ጀምረዋል፡፡
  3/ የመንግሥት ሠራዊት ሁሉም ቀበሌዎችን እየከበቡ ግለሰብ ሳይለይ በጅምላ ከልጅ እስከ አዛውንት ድረስ በዱላ እና በሰደፍ እየቀጠቀጡ ወደ ማሰቃያ ሥፍራዎች ይወሰዳሉ፡፡ ይህ ድርጊት የአንድ ቀን ብቻ ቢሆን መልካም ነበር ግን ሠራዊት እና ኪራይ ሰብሳቢ አመራሮች በጋራ ተቀናጅተው በሁሉም ቀበሌዎች ስምሪት ወስደው እዚያ መኖር ከጀምሩ ብዙ ወራቶች ሆኗል፡፡ ከዚህ የተነሳ ጠቅላላ የየቀበሌዎቹ ነዋሪዎች መኖሪያቸው ለቅቀው ኑሮ ጫካ አድርገዋል፡፡ በየጫካ ሕክምና በማጣት÷በረሃብና ጥም÷በወልድ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቤት ይቁጠረው፡፡ በዚህ ብቻ ብያበቃ ጥሩ ነበር ነገር ግን የክልሉ ቡድን በገንዘብ በገዛቸው ጠቋሚዎች አማካይነት ሠራዊቱን አስከትለው እስከ ጫካ በመምጣት የሚገድሉትን እየገደሉ የሚፈልጉትን ወደ ፊት ላይጠቅም በዘግናኝ አካላዊ ድብደባ ወደ ማጎሪያ ቤቶች ይወስዳሉ፡፡ እዚያም ሕክምና አይታሰብም፡፡
  4/ በየገጠርቱ ያሉ ሁሉም ት/ቤቶች እና ጤና ተቋማት ተዘግተው እነዚያ መሥሪያቤቶች የወታደር ካምፕ ሆነዋል፡፡ በጣም የሚያሳዝነው የፖልትከኞቹ ድራማ ግን ት/ቤቶች አገለግሎት እየሰጠ መሆኑን ለማስመሰል በውስን ት/ቤቶች ባንድራ ብቻ እያውለበለቡ ይገኛሉ፡፡ እውነታው ግን በካራት ሙሉ 1ኛ ደረጃና ካራት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ት/ቤት ውስጥ ሃምሳ የማይሞሉ የኮንሶ ዘጎች ያልሆኑ ተማሪዎች ቢመዘገቡም እነሱ ራሳቸው በአግባቡ እየተማሩ አይደሉም፡፡
  5/ ዜጎች በስደት ላይ እያሉ ብዙ ሴቶች የኮንሶ ባህል በእጅጉ የሚፀየፈውን አስገዲዶ መድፈር በሠራዊቱ አማካይነት ይፈፀማል፡፡
  6/ የጅምላ እስራትም በሁሉም ቀበሌዎች ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ፆታና ግለሰቦችን ሳይለይ ከሕፃናት እስከ አዛውንት ድረስ ተቀጥቅጠው ይታሰራሉ፡፡ ለአብነት ብቻ ትላንት 26/3/2009 ዓ.ም ኮልሜ አገልግሎት የተከሰተውን አንዱን ሰብዓዊነት የጎደለውን ድርጊት ላስታውሳችሁ-የአመራሩ ምስት ከወለደች አራት ቀን ቢሞላትም ሠራዊቱ ባነሳው ሽብር የተነሳ ቤቷን ለቅቃ በአከባቢው ባለ ደሳሳ ጎጆ ውስጥ ከጨቅላ ሕፃኗ ጋር ተጠቅልላ ባለችበት በድንገት ሠራዊቱ ዓይን ሥር ገብታ እየተቀጠቀጠች”ባልሽ የት ነው ያለው” ስትባል “የት እንዳለ አላውቅም” ብላ ስትመልስ “ባልሽ ሕፃኑን ያምጣ” ብለው እሷን ብቻ ወደ ኃላ አስረው ወደ ካራት ከተማ ለእስር አመጧት፡፡በየቦታ የታሰሩ እስረኞች ከ 3ሺህ በላይ ይደርሳል ተብሎ ይገመታል
  7/ በመጀመሪያዎቹ አከባቢ የኮንሶ ወረዳ አንዱ ቀበሌ የሆነውን አባሮባ ሕዝብን ለሁለት ከፍለው ሰባት መንደሮችን በመያዝ ነዋሪዎች እና ሠራዊቱ በጋራ ሆነው ሁለት የቀበሌን መንደሮች ለመዋጋት ተነስተው የአንዱን መንደር “አማራይታ” ነዋሪዎችን ተዋግተው ብዙ ሰዎችን ከገደሉ በኃላ ቤቶቹን ሙሉ በሙሉ አቃጥለው ወደ አመድነት ቀይረዋል፡፡ ቅርብ ጊዜ ደግሞ ቀሪውን መንደር”ኮርማሌ” ነዋሪዎችን ተዋግተው የተወሰኑ ቤቶችን አቃጥለዋል፡፡ በዚህ ብቻ ሳያበቃ በሠራዊቱ ሥር ያሉት መንደሮች ከልዮ ሀይሎች ጋር በመተባበር ለአባሮባ አጎራባች ቀበሌዎችን(ጌራ÷ካሻሌ÷መጨቀ) በከባድ መሣሪያ እየተዋጉ አያለ ሰዎችን በመግደል ንብረቶችን አቃጥለዋል እስከ ትላንት ድረስ ትንኮሳውን አልተውም፡፡ በዚህ ሁሉ ግን የባለሥልጣናት ቡድን እነኚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ሌሎችም ያልተጠቀሱ በርካታ ወንጀሎች እየሠሩ ጥፋቱን ወደ ሌላ አካል “ባህላዊ ቡድን” እያሉ ማባበያ ይሰጣሉ፡፡ “ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ” ይሉታል፡፡
  ይህ በዚህ እንዳለ ኮንሶ በአሁኑ ወቅት የጥንት ዳርፉር ትመስላለች፡፡በሠራዊቱ ከሚገደለው ውጪ ሰዉ በየቦታው ሞቶ ይቀራል በማን እንደተገደለም አይታወቅም፡፡
  የደርግ መንግስት የሀገርቷን ዳር ድንበር ለማስጠበቅ አንድን ግለሰብ ብቻ አሳምኖ ወይም አባሮ ይይዛል እንጂ እንደዚህ ዓይነት አፀያፊ በደሎች በጠቅላላ በኮንሶ ላይ ፈጽሞ አያውቅም፡፡ ከአባቶቻችን በታርክ እንደምንሰማው ከደርግ በፊትም የነበሩ መንግሥታት የኮንሶ ሕዝብን እንደዚህ ፊዳ አሳይቶ አያውቅም፡፡ ወደ ፊትም ማንኛውም ማካካሻ ሥራ ለሕዝቡ ቢደረግም ምሁሩም ሆነ አርሶአደሮቻችን የደረሰበትን በደል ፈጽሞ አይረሳውም፡፡ ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ዕድሜ ከሰጠን አብረን የሚናየው ጉዳይ ነው፡፡
  በዚህ ሁሉ ግን ሕዝቡ ትላንት ሕገመንግሥታዊ ጥያቄውን አጥብቆ እንደያዘ ሁሉ ነገም ቢሆን እስከ መጨረሻ ኢሰብዓዊ በደሎችን በፀጥታና በሰላማዊ መንገድ እየተቋቋመ ሕገመንግሥቱን በመጠበቅ ለመብቱ በጽናት ይቆማል፡፡
  ነፃነትና ፍትህ ለጭቁኑ ኮንሶ ሕዝብ !!
  ለአፍታም ቢሆን ጥያቄያችን አይቋረጥም!!
  የኮንሶ ሕዝብ ፍትህ ፈላጊ እንጂ አሸባሪ እና ግንቦት 7 አይደለም!!

 2. Kahana Lemita

  ቀን 15/3/2009 ዓ.ም
  በደቡብ ኢትዮጵያ ኮንሶ ወረዳ ውጥረቱ እንደነገሠ ነው።
  በደኢህዴን እና የእነሱ ቅጥረኛ በሆኑት ትናንሽ የሰፈር አምባገነኖች ምክንያት የማንነት እና ዘር የማጥፋት(Genocides) አደጋዎች ከፊታችን
  ተደቅኖብናል፤ ከዚህ በፊትም በስውር ሲፈፀምብን ነበር፡፡
  ኮንሶ ወረዳ ከዚህ በፊት በደቡብ ኢትዩጵያ ከሚገኙት 8 ልዩ ወረዳዎች ውስጥ አንዷ ነበረች፡፡ሽፋራው ሽጉጤ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ጉዳዮ የሚመለከታቸው የተለያዩ የኮንሶ አካላት ሳይመክሩበት ሕዝቡ በሰገን ዞን ሥር እንዲተዳደር በወታደራዊ ጉልበት ተጭኖ ነበር። በማዕከላዊ እስታቲስቲክስ ዳታ መሰረት ከአስር ዓመት በፊት በተካሄደው አገር አቀፍ ምርጫ የወረዳው ሕዝብ ብዛት ወደ 306,000(ሶስት መቶ ስድስት ሺህ) የሚያክል ብዛት አላት።
  ይህንን የሚያክል ህዝብ ይዛ ቀድሞውንም ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ በወረዳ ደረጃ በመዋቀሯ ምክንያት የአካባቢው ህዝብ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት በአቅራቢያው ባለማግኘት ምክንያት ምን ያክል በከፋ ስቃይ ውስጥ እንደነበር መገመት አያዳግትም። በነገራችን ላይ እንደ አጠቃላይ ከተመለከትን የደቡብ ኢትዩጵያ ህዝቦች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ሁሉም ክልሎች ሲነጻጸር በመሰረተ ልማት ዝርጋታና በእድገት የመጨረሻ ደረጃ ላይ እንደሆነ ወርልድ ባንክን ጨምሮ ሌሎች የአለም አቀፍ ድርጅቶች ከአንድ አመት በፊት ሪፖርት ማውጣታቸውን አስተውሳለሁ ። ይህ ችግር ግን በኮንሶ አከባቢ በእጅግ መስተዋሉ የዓይን እማኞች ነን፡፡በኮንሶ ወረዳ አንድ ገበሬ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለማግኘት በአማካይ የ6 ወይንም የ7 ሰዓት መንገድ በባዶ እግሩ መጓዝ ይጠበቅበታል። ደርሶ መልስ ባላጋንን የ13 ሰዓት መንገድ። ለዛውም በየአካባቢው በደኢህዴን መስፈርት የተሾሙት ትንንሽ መሳፍንቶችን ግልምጫ እና ስድብ ለማስተናገድ። ወደ ዋናው ጉዳይ ስንመጣ ሕዝቡ አዎንታዊ ምላሽ ሳይሰጥ የተቋቋመው ዞን በአራት ዓመት ውስጥ የኮንሶን ዕድገት እንደ ግመል ሽንት ወደ ኃላ የጎተተ በመሆኑ ሕዝቡ ከዚያ ቀንበር ለመውጣት ብዙ የምክክር መድረጎችን በማካሄድ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ይዞ የፍትሕ ያለህ የሚል ጩሄት ለክልልና
  ፌደራል መንግስታት ማስተጋባት የጀመሩት ከዛሬ አንድ ዓመት በፊት ነበር።
  እርግጠኛ ሆነን የሚንናገረው የልማት እና ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ማቅረብ
  የተጀመረው በዚህች አንድ ዓመት ውስጥ ብቻ ሳይሆን ዞኑ እንደተመሠረተ ነበር፡፡አሁን በዚህ 16 ወራት ውስጥ እያየለ የመጣው የኮንሶ ህዝብ ጥያቄዎች በአይነቱም በይዘቱም ጠንከር ያሉ ናቸዉ፡፡በቅርቡ የተመሠረተው ሰገን ዞን
  ደቡብ ክልል ውስጥ 13 ነባር ዞኖች እና 8 ልዩ ወረዳዎች ባሉት ላይ አንድ አድስ ዞን ተጨምሮ 14ኛው ዞን ሆኗል፡፡
  የሰገን ዞን ከተመሠረተ በኃላ ከዚህ ቀደም በኮንሶ
  ወረዳ ክልል ውስጥ የነበሩ በርካታ ቀበሌዎች በግዳጅ ወደ ሰገን ዞን እንዲካለሉ ተደርጓል። በዚህም ምክንያት የኮንሶ ማንነት በኃይል በማስካድ ያልታወቀ በቅርቡ በመጣ ሰገናዊ ማንነት በኃይል የማጥመቅ
  ስራ እየተሰራ ይገኛል። ሌላኛውና ሁለተኛው አንኳር ጥያቄው 306,000 በላይ ህዝብ ሆነን ሳለ በአንድ ወረዳ መስተዳድር ስር መዋቀራችን ተገቢ አይደለም፡፡ ቀድሞንም በዞን ደረጃ መሆን ነበረብን ሰለዚህ መንግሥት ያለውን የህዝብ ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የዞን ማዋቅር ሊሰጠን ይገባል የሚል ጥያቄ ነው።
  እነዚህንና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ያነገበው የኮንሶ ህዝብ በሰለጠነ አኳኃን ሰላማና ህዝባዊ ትግል ከጀመሩ ዓመት በላይ አስቆጥረዋል። በተደጋጋሚ ጊዜ የአካባቢው ተወካዮች ወደ ክልልና ፌደራል መንግሥት ተንቀሳቅሰዋል።
  ይሁንና የዴኢህዴን ከፍተኛ መሣፍንቶች በተቃራኒው ጥያቄውን ለማዳፈን የክልሉን ልዩ
  ኃይል፣ የፌደራል ፖሊስ ፣በደቡብ ክልል የፀጥታ ኃይል ዩኒፎርም ጭንብል አጋኣዚ እና የመሳሰሉትን ታጣቂዎች በአካባቢው ማራገፍ ነው
  የሆነው። እስከ አሁን ድረስ ብዙ ሰዎች በጥይት ተደብድበው ተግድለዋል በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችም በተለያዩ ሥፍራዎች ታጉረው ስቃይ እየተደረገባቸው ነው፡፡ በከተማና ገጠርቱ የሚኖሩ ኮንሶዎች በሠራዊቱ ወከባ የተነሳ ኑሮን ጫካ ካደረገ በርካታ ወራቶች አስቆጥረዋል፡፡ትግሉ ግን አልቆመም ፍጽሞ የሚቆምም አይነት አይደለም። እጅግ በጣም የሚያሳዝነው በአሁኑ ሰዓት የኮንሶን ህዝብ መንገድ በመምራት እና ልዩ ልዩ እርዳታ በማድረግ እያሰጨፈጨፉና እያሰቃዩ የሚገኙት ከኮንሶ አብራክ የወጡ የአካባቢው ተሿሚዎች መሆናቸው ነው።
  በኔ እይታ ከኮንሶ አብራክ የተውጣጡ ተሿሚዎች ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት በአሁን ሰዓት ለአካባቢዬና ለህዝቤ ነፃነት እታገላለሁ ለሚሉት እና ለተከታዮቻቸው በተጨማሪም ከእርሱም ፍጹም ነፃነት በመሻት ላይ ላሉ ሁሉ ትልቅ መልእክት አለኝ። ትናንሽ መንግስታትን በአንድም በሌላ መልኩ እየተደራጁ በመፍጠር
  መካከለኛውንና የበታችኛውን የህብረተሰብ ክፍል ወደ ታች ደፍጥጦ በመያዝ መዝረፍ እና ደም ዕምባ ማስለቀስ እንዳልሆነ እረዳለሁ።
  ነፃነት ለጭቁኖቹ!!!

Leave a Comment