October 7, 2016 at 7:40 am #589
Profile photo of GebreyesusGebreyesus
Moderator

ዜና ትንታኔ በኮንሶ
በኮንሶ ላይ ዉጥረቱ እንደቀጠለና ህዝቡም ገሀዱ ካልወጣ ማለቱን ቀጥሏል
መስከረም 16/2009 ዓ.ም
ህገ-መንግሥቱን በተግባር ለመተርጎም ያልፈለገዉ እና በአንድ የብሔር የበላይነት ሀገርቱን ሊያሽመደምዱ የቆሙት የኢህአዴግ አመራር ነን ባዮች ዛሬም በኮንሶ ላይ ዉጥረቱ እንድቀጥል አድርገዋል፡፡ የኮንሶ ህዝብ በ2003 ዓ.ም ከልዩ ወረዳ ወደ ወረዳ ዝቅ ካለበት ጊዜ ጀምሮ ተቃዉሞዉን በተለያየ መንገድ ቢያሰማም ሰሚ አካል እንዳልነበረዉ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ በኮንሶ በኩል የቀድሞዉን ዞን መስራች የነበሩት ሰዎች መካከል አቶ ገለቦ ጎልቶሞ የወቅቱ የል/ወረዳዉ ዋና አስ/ዳሪ ፣ ዳዊት(ኦራኖ) ኩሲያ በወቅቱ የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊና ዘርፌ ብዙ ሥ/ሂ/ባለቤት ፣ ግለኖ ተገኝ በወቅቱ በደቡብ የኦሞ ማይክሮፋይናንስ ኃላፊና የዳዊት(ኦራኖ) ኩሲያ አጎት ፣ ማቴዎስ ገለቦ የክልሉ አርብቶ አደር ኃላፊ እና ሌሎች አንዳንድ የወረዳዉ ርካሽ ተወዳጅነትና ሥልጣን ፈላጊዎች አመራሮች ነበሩ፡፡ በጊዜዉ ዳዊት(ኦራኖ) ኩሲያ አሁን በቅጽል ስሙ በአካባቢዉ መጠሪያ ጮልታ(እውር) የሚሉት የተሻለ የሥልጣን ቦታ ለማግኘት ከገለቦ ጎልቶሞ ጋር ቀበሌ ለቀበሌ በመመላለስ ህዝብን ለማሳመን ሲሯሯጡ ነበር፡፡ ቅርብ ጊዜ በዶቼበሌ ሲናገር እንደሰማችሁት ህዝቡ አሮገዉ ዞን ሲደራጅ እንደተስማማ ይገልጻል፡፡ ሆኖም ግን ቀበሌያቶች ገብተዉ በድንጋይ የተባረሩባቸዉ መካከል ቡሦ ፣ ኮልሜ ፣ ፋሻ እና ሌሎችም ቀበሌያቶች ላይ ያለምንም ተቀባይነት ወጥተዋል፡፡ እናም ከዚያ በኋላ የኮንሶ ህዝብም ሆነ ም/ቤት በዞን አወቃቀሩ ላይ የአዎንታ ዉሳኔ አይደለም ንግግር ሳያደርግ ልባቸዉ የፈቀደዉን በማድረግ በዉሸት ፋብሪካቸዉ በመጠቀም ህዝቡ እንደተስማማ አድርገዉ ጨርሰዋል፡፡ ያም ሆኔ ይህ ግን ካለዉ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ዉሳኔዉን የተቀበለ ህዝብ ዛሬ ላይ አንድ ዓመት ከሁለት ወር ሙሉ እንደማያስቸግር ለማንም መገመት አያዳግትም፡፡
በኮንሶ ላይ እየደረሰ ያለዉ ጫና ፣ ድብደባ ፣ ግድያዉና እስራቱ አሁንም ቀጥሏል፡፡ ሰሞኑን በተያያዙት የዉሸት ፋብሪካ ምርቶቻቸዉ ሀገርን በዉሸታቸዉ የማሸበር አድማቸዉን ተያይዘዉታል፡፡ ከዚህ በታች የተጠቀሱት እዉነታዎች ጨፍጫፊዎቹ ቢያስተባብሉም የአማራም ፣ የኦሮሞም እና የኮንሶዉም ህዝብ የእኔ ስለሆኔ ስለህዝቤ ስለሚያገባኝ የሰማሁትንና ያየሁትን ከመተንፈስ ወደኋላ አልልም፡፡ ሰሞኑን እንድህ ነበር አሸባሪዉ የደቡብ አመራሮችና ልዩ ሀይሎች ከፌደራል ፖሊስና መከላከያ ጋር በመተባበር እንደሁም ሌሎች የኮንሶ ም/ቤት የማያዉቃቸዉ የአካባቢዉ ከሀዲ አመራር ነን ባዮችን በመጠቀም የልዩ ሀይሉን ሚሊተሪ ለብሰዉ በመመሳሰል ከተማ ላይ ሰዎችን አሳድደዉ እያሰሩ በየቀበሌዉ ቤት ለቤት በመግባት ልጆችን በመደብደብ ወጣቱና አዋቂን ሲያዩ እየቀጠቀጡ ወስደዉ በማሰር ሲተባበሩ የቆዩት እና መጠቀሚያ ዕቃ የሆኑት አቶ ጉራሾ ለሚታ ፣ ያበሎ ኩሲያ ፣ጋሻዉ ኩሲያ ፣ ጉደኖ ያሊሳ ፣ አለማየሁ አያኖ ፣ ከበደ ካዮላ ፣ ሳሙኤል ገለቦ ፣ ካምብሮ አዘጋጅ ፣ዘርፉ ላቀዉ ፣ ጋሻዉ ካስሜ ፣ ገልገሎ ኦርካይዶ ፣ ሀላጌ ኮይርታ(ካንጋሮ) ፣ዘይሴ ካንሾሌ ፣ ወፍዘራሽ ድቃላዉ አቡጠጄ (ንጋቱ መንገሻ) ፤ ገረመዉ አያኖ ፣አርጋቸዉ አያይቶ ፣ገረሱ ካታሌ ፣ ኩሴ ቢሴ ፣አረሮ ጋማይዳ ፣ኤረኬ ገየቶ ፣ገዝሀኝ ኦዳ ፣ኡርማሌ ኡጋንዴና ሌሎችም ናቸዉ፡፡ እየሆነ ያለዉ ሳያንስ አሁንም ቢሆን የእስራትና የድብደባ አልፎም የግድያን ሰንሰለት በማበጀት ህዝቡን ለስብሰባ እንድወጣ በማይክራፎን ይለፈልፋሉ፡፡ ወንድም እየሞተ ፣እየተረገጠ ፣እየተደበደበ ፣ያለምንም ጥፋት እየተገደለ ከገዳዩና ከአጥፊዉ ጨፍጫፊ አካል ጋር እንዴት እንሰብሰብ? ወገን ለስብሰባ ተብሎ ተወስዶ እየታሰረ ፣ በእስር ቤት ዉስጥ የድብድብ መለማመጃ ሆኖ ተጎድቶ ሳይታከም እየሞተ ጠያቂ ባጣበት እንዴት እንሰብሰብ? ህዝቡን ከመኖሪያ ቀየዉ አሳድዶ በአፌሙዝ ቀበሌያቶች በተከበቡበት እንዴት እንሰብሰብ? ሳትወዱ በግድ ለዉሸት ተገስታችሁ ኑሩ ፣ሠላም ነዉ በሉ ፣በግድ ለሰይጣን ዞን ተገዙ ፣ከደደብ ክል ጋር ቀጥሉ እየተባለ ባለበት እንዴት እንሰባሰብ? ስለዘህ ህዝቡ እስከዛሬ ላለመሰባሰብ የወሰነበት ከዚህ በላይ የተጠቀሱት ጥያቄዎችና ሌሎችም ባለመመለሳቸዉ ነዉ፡፡ ተሸፍኖ ስብሰባ ስብሰባ ቢባልም የ30 ሰዉ በላይ ህይወት ጠፍቶ ረሳቸዉ እንኳን ህዝቡ በተከለከለበት በመንግስትና ማህበራዊ ሚድያዎች መሬት ላይ ጠብ ያላለ ነገር እየተወራ ከነዉሸታችን ተቀበሉን ብሎ ማለት የማይቻል መሆኑን ማንም እንድገነዘብ ህዝቡ ይፈልጋል፡፡
ሌላኛዉ ልፈፋቸዉ መንግሥት ሠራተኞች ወደ ሥራ እንድመለሱ ፣መ/ቤቶች እንደሚከፈቱና ሌቦቹ አመራሮች ከነሌብነታቸዉ ወደ ሥራ እንደሚመለሱ ነዉ፤፤ ሲጀመር የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ከእዉነት መሠረት ላይ የተነሳ በፍጹም ሠላማዊና ህገ-መንግስታዊ በሆነ መንገድ ለማስከድ የተጀመረ ጥያቄ ነዉ፡፡ ነገሮች ከ2003 ዓ.ም የሰገን(ሰይጣን) ዞን ምሥረታ ጀምሮ በየጊዜዉ እንደተረገዘ ልጅ ቀስበቀስ እያደገ ሐምሌ ወር በ2007 ዓ.ም ላይ ጎልቶ ቢወጣም ጠንከር ያለ ህዝባዊ መሠረት ያለዉ ጥያቄ ነዉ፡፡ ለዚህም ነዉ የብሔሩ ተወላጅ ከነግድፈቶችና ጥቅሙ ህብለተሰቡን ያለ በጀት በነጻ ለማገልገል የተነሳዉ፡፡ በሠላማዊ መንገድ የተጀመረዉ ትግል በደቡብ ክልል ለመበጥበጥና ለመቀልበስ የተለያዩ ሙከራዎች ቢደረጉም የኮንሶ ህዘብ ሁሉን በትዕግሥት ችሎና ተቻችሎ ገፍቷል፡፡ ምሁሩም በፊናዉ ለህብረተሰቡ አገልግሎት እየሰጠ ባለበት ግንቦት ወር 2008 ዓ.ም የፋይናንስ ጽ/ቤትና ምክትሉ ህዝቡ ያልተጠቀመዉን በጀት የ5.6 ሚሊየን ብር ቼክ አጽፈዉ በሥርቆት ሊያወጡ ሲሞክሩ ተይዘዉ በቁጥጥር ሥር ዉለዋል፡፡ ስፒል እንኳን ከንብረቱ እንድጠፋ የማይፈልግ ህዝብ እነዚህ ሌቦች የፌደራል ፖሊስ በተገኘበት ሌብነታቸዉን አምነዉ በቃለ-ጉባኤ ተይዞ ወደሚመለከተዉ ክፍል እስከ ፌደራል በጽሑፍ ተደግፎ ቢወሰድ ኑና መ/ቤቶቹን ዝጉልን የተባለ ይመስል የደቡብ ክልል የወረዳዉን ፋይናንስ ግቢ ዉስጥ ያሉት ሁለት መ/ቤቶች ንግድ እንዱስትሪና ገቢዎች ጽ/ቤት እንድሁም ፋይናንስ ጽ/ቤትን ጨምሮ በክልሉ ልዩ ሀይል እንድጠበቅና ሠራተኞችም ወደ ግቢ እንዳይገቡ ተደረገ፡፡ በመቀጠልም የሦስቱ መ/ቤቶች መዘጋት የሀገር ገቢ እንዳይሰበሰብ ብሎም የጤና ተቋማት በህጋዊ ደረሰኝ ብቻ ገቢ እየተሰበሰበ የህክምና አገልግሎት ስለሚሰጥ ለመዘጋታቸዉ ምክንያቱ የመ/ቤቶቹ በመንግሥት ኃይል መዘጋት ነዉ፡፡ የመ/ቤቶቹ መዘጋት በዚህ ሳያበቃ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ከግንቦት ወር 2008 ዓ.ም ጀምሮ ሳይከፈል ሠራተኞች ህዝባቸዉን ለማገልገል በገቡት ቃል መሠረት መገኘት ስለነበረባቸዉ ሌሎች መ/ቤቶች ጭምር እንዳይገባ አጋጣሚዉን በመጠቀም ወደ ዓይናቸዉ የገባ ሁሉ ሲያስሩ ሠራተኛዉ ሥራዉን ለማቆም ተገድዷል፡፡ ለዚህም ነዉ ዛሬ ላይ የኮንሶ ህዝብ ልጁን ይዞ ከራሱ ጋር ያለዉን እየተካፈሌ የአባቱን ጓሮ እንድቆፍርና ከቤተሰቡ ጋር እንድኖር ያደረገዉ፡፡ ከዚህ በኋላ የኮንሶ ህዝብ ከሌቦች ጋር ለመኖርም ሆነ ለመሥራት እንድሁም ከ5 ወር በኋላ የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ቢሠራም እንኳን ሰሪዉ ማነዉ? ፈራሚዉ ማነዉ? የሚሉ ጥያቄዎች ከሌቦቹ ጋር ከነሌብነታቸዉ መቀጠል ስለማይቻል መመለስ አለባቸዉ፡፡ ሠራተኛዉ ወደ ሥራ እንድመለስ የሚለፈፈዉ ከማን ጋር ለመሥራት? በምን ተስፋ? ከምን መነሻ? የሚሉት ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባቸዉ፡፡ አለበለዚያ ግን አይጥ በሥጋ እንደሚያዝ ለወጥመድ የተዘጋጀዉ በደመወዝና ወደ ሥራ በመመለስ ምክንያት ማንንም የሚያስብ አዕምሮ ያለዉን የኮንሶ ልጅ እንደ አይጥ በወጥመድ ለመያዝ የታሰበዉ የተነቃባቸዉ መሆኑ ታዉቆ የኮንሶ ልጅ በደመወዝ ብቻ ተደልሎ የሚኖር መስሎ እንዳይታይ ማንም ሊገነዘብ ይገባል፡፡
ሌላኛዉ ልፈፋቸዉ የዞን ጥያቄ ተመልሷል የሚለዉ ነዉ፡፡ ጥያቄዉ በሚገባ መስመሩንና ህጉን ጠብቆ እየሔደ ባለበት ሁኔታ ለማደፍረስ ብዙ ጥረቶች ተደርገዋል፡፡ በመጀመሪያ እንዳይደፈርስ በተሰሩት ሥራዎች ስከታማ ዉጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ክልሉ እንደ ክልል ጥያቄዉን አይቶ የራሱን ዉሳኔ ቢያስተላልፍም የኮንሶ ህዝብ ዉሳኔዉን በመያዝ ለፌደራል መንግሥት ይግባኝ አቅርቦ አፈጻጸሙን እየጠበቀ ባለበት የጥይት እሩምታን በህዝብ ላይ እያዘነቡና እየገደሉ ለጥያቄዉ መልስ ተሰጥቷል ማለት እንኳን የኮንሶ አዋቂ አርሶ አደር ከኮንሶ የተወለደ አንድ ቀን ያልሞላዉ ጨቅላ ህፃን ሊሸወድ እንደማይችል ለማንም ግልጽ ሊሆን ይገባል፡፡ በህዝቡ ላይ ከደረሰዉ ጫናና እንግልት ግድያን ጨምሮ በጣም የከፋ ስለሆነ አንገት ቢቀነጠስ ከዚህ ክልል ጋር ለመቀጠል እንደማያዋጣዉና ከዚህ በኋላ የክልሉ ልማትም ሆነ መንግሥት ምንም ለዉጥ የማያመጣ መሆኑን ስለተረዳ ህዝቡ በህጉ መሠረት ሌሎች አማራጮችን ለመጠቀም ይገደዳል።

በትናንትናው ዕለት ከህዝብ ተወካዮች አቶ ገዛኸኝ ካላ ፣ አዳኔ ዝናቡንና ገመቹ ካሻርቶን በቁጥጥር ስር ቢያዉሉም ሕዝባዊ ትግላችን ይቀጥላል፡፡
ፀረ-ህዝብ አገዛዞችንና አካሄዶችን በጽናትና በትጋት አጥብቀን እንታገላለን፡፡