View Post

የአርቲስት አፍሪካ ለማ አዲስ የሙዚቃ ሲራ Hip-Hop በኮንሰኛ

In Audio by Konso People0 Comments

አርቲስት አፍሪካ ለማ አዲስ የሙዚቃ ሲራ ይዞ መጣ:

አዝናኝ በሆኑ ግጥሞቹ የሚታወቀው አርቲስት አፍሪካ ለማ እስካሁን በኮንሶ ታርክ ታይቶ በማይታወቅ አዲስ የሙዚቃ ስልት ራፕ  ወይም (ሂፕ-ሆፕ)  ከሙያ ባልደረባው አርቲስት ሠራዊት ዲባባ ጋር አድስ ነጠላ ዜማ ይዞ ቀርቧል፡፡ ይህ የሙዝቃ ስራ በሁሉም ደረጃ የተዋጣለት ሲሆን በኮንሶ ልጆች መሰራቱ እጅግ ልዩ ያደርገዋል፡፡

በ አሁን ሰዓት በዓለምአቀፍ ደረጃ በ1ኛነት እየመራ ባለው የ(Hip-Hop)  ሙዝቃ ስልት የኮንስኛ ሙዝቃ መሰራቱ ለቋንቋው እድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማበርከቱም በላይ የኮንሶን ባህልና ማንነት ለአለም ህዝብ ያስተዋውቃል፡፡

በመላው ዓለም ላላችሁ የኮንሶ ተወላጆች፡-

ይሄ የሙያ ዘርፍ እንዲያድግና እንዲጎለብት አርቲስቶቹ የሙያና የገንዜብ ዲጋፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡

 

ሙዚቃውን ከዚህ በታች ክልክ በማድረግ ያጫውቱ

View Post

የዲቪ አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መመዘኛዎች

In Uncategorized by Konso People0 Comments

እባክዎ በጥንቃቄ ያንብቡት!

 1. የመጀመርያ ማመልከቻ በምሞሉበት ወቅት ማመልከቻዎ
 • ባለቤትዎ(ባል/ሚስት)
 • ከ21 ዓመት የሆኑ ልጆችዎን ስም ማስፈር አለብዎት
 1. ከሚከተሉት ውስጥ አንዱ የትምህርት ማስረጃ ሊኖርዎት ይገባል
 • የሁለተኛ ደረጃ ትም/ት (12ኛ ክፍል)መልቀቂያ ሰርተፍኬት፡ 5 የትም/ት ዓይነቶችን ያለፉበት የሚያሳይ ወይም
 • 4 ዓመት የዩኒቨረሲቲ ትም/ት ያጠናቀቀ
 • ማሳሰቢያ፡ – የ TVET  ወይም  10+3 የትም/ት ማስረጃ ለዲቪ ተቀባይነት የለውም፡፡
 1. ልብ ይበሉ፡ ተፈላጊውን የትም/ት ደረጃ የማያሟሉ ከሆኔ ብቁ ሊያደረግዎ የሚችል የስራ ልምድ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በስራ ልምድ ብቁ ለመሆን ባለፉት 5 ዓመታት ውስት በቋሚነት ለሁለት ዓመታት በሙሉ የስራ ሰዓት፡ የሁለት ዓመት የኮሌጅ ስልጠና በሚፈልግ የስራ ዓይነት ላይ ተሰማርተው የቆዩ መሆን ይኖሪባቸዋል፡፡
 • ከላይ የተጠቀሱትን የትም/ት ደረጃ የማያመበ https://www.onetonline.org/ ላይ እንደተገለፀው ለዲቪ ብቁ የሚያደርጉ የስራ ዓይነቶች በልዩ የሙያ ዝግጅት ስልጠና (SVP) የተብራሩ ሲሆን የአመሪካ የሰራተኛና የሥራ ብቃት ዝርዝር በዞን 4 ወይም 5 የተመዘገቡ ስራዎች 7 ነጥብና ከዝያ በላይ የተሰጠው መሆን ይኖሪበታል፡፡
 1. ከማመልከቻው በፊት ለዲቪ የሚሆን ጉርድ ፎቶ በባለሙያ የተነሳ ከፎቶ ቤት በ ፈላሽ ድስክ ወስደው ለኦንላይን ምዝገባ ዝግጁ ማድረግ ይኖሪቦታል፡፡ ፎቶዉን ፕርንት አያድረጉ፡ በፉላሽ/በሲዲ ከፎቶ ቤት ይቀበሉ
 2. ለጠቅላላ እውቀት ይሄን የማመልከቻ መመሪያዎች ቪዲዮ ይመልከቱ፡፡ የዲቪ አሞላል አንድ በአንድ ያሳያል

https://www.youtube.com/watch?v=tOQlh2d2EbQ&feature=youtu.be

ምዝገባው አሁን የጀመረ ሲሆን፡-

 1. https://dvlottery.state.gov/(S(5mz4lykayh0wt0i1aqszluvi))/default.aspx ላይ ክልክ በማድረግ ይጀምሩ
 2. ጥያቄ ካለዎት ዲቪ ለኮንሶ ህዝብ የሚለውን የፈስቡክ ገጽ ላይክ በማድረግ እዛ ላይ ፖስት ያድርጉ፡፡ አፋጣኝ ምላሽ ያገኛሉ፡፡
 3. የኢመይል አካውንት የለላችሁ የ ጂመይል አካውንት እንዲታወጡ እናበረታታለን፡፡
 4. የኮንሶ ልማት ማህበር ፖስታ አድራሻን ይጠቀሙ፡፡ በተለያዩ ዩኒቨረሲቲ የሚትገኙ ተማሪዎችም ቢሆን ተመሳሳይ የኮንሶ ልማት ማህበር የፖስታ አድራሻ ብትጠቀሙ በቀላሉ ወደ እናንተ ይደርሳል፡፡
View Post

Dv lottery for Konso people የዲቪ ሎቴሪ ለ ኮንሶ ህዝብ!

In Link, Standard by Konso People0 Comments

ይህ እድል ለብዙ ዓመታት የሁላችንንም በር ሲያንኳኳ የቆየ ቢሆንም በተለይ በኮንሶ አካባቢ ላለን ወጣቶች ከግንዛቤ ና መረጃ እጥረት የተነሳ ብዙ እድሎች አምለጠውናል፡፡ ይሄን ለማለት ያነሳሳኝ በተለያዩ የአሜሪካ ስተቶች ያሉ ኢትዮጵያዊያን ቁጥር አጀብ የሚያሰኝ ነው፡፡ በተለይ በዋሽንግተን ዲሲ አማርኛ የስራ ቋንቋ እስኪሆን ዲረስ እድሉን መጠቀም ችለዋል፡፡ ሆኖም ከኮንሶ አካባቢ የአመልካች ቁጥር በጣም አናሳ በመሆኑ ምክንያት በጣት የሚቆጠሩ የኮንሶ ልጆች የእድሉ ተጠቃሚ ሆነዋል፡ የአመልካች ቁጥር እዱሉን ካገኙት የኮንሶ ልጆች ጋር ቢሰላ ውጠቱ የሚያሳየው ከፍተኛ የማግኘት እድል እንዳለ ነው፡፡  የ2019 ዲቪ ሎተሪ ዛሬ ኦክቶበር 3 2017 ይጀምራል ፡፡ አባካችሁን ከዝህ በታች ያለውን ድህሬ-ገፅ በመከተል ማመልከቻውን በዝህ ሁለት ሳምንት ውስጥ እንዲትጨርሱ በአክበሮት እጠይቃችኋለሁ፡፡

ከዝህ በታች ትክክለኛ የሆኑ ሁለት ድህሬ ገጾች ይገኛሉ 1ኛው ለማመልከት ብቸኛው አማራጭ ነው፡፡ ለሎች ፈክ ድህረገጾች ስላሉ ይጠንቀቁ :: እነዲሁም ምንም አይነት ክፊያ የሚጠይቅ ድህረ-ገጽ ፈክ(የውሸት) መሆኑን ከወድሁ ይታወቅ፡፡ 2ኛው እያንዳነዱን የማመልከቻ መመሪያ ዝርዝር ይዟል በደንብ ያንብቡት፡፡

ማመልከቻ ድህሬ-ገጽ

 1. https://dvlottery.state.gov/(S(qyvxonx3lwkytuda5t5aa1xz))/default.aspx

የማመልከቻ መመሪያዎች

2. https://travel.state.gov/content/visas/en/immigrate/diversity-visa/instructions.html

መልካም እድል ለኮንሶ ህዝብ!

 

View Post

ኮማንድ ፖስት በማንነት ጥያቄው ምክንያት በየጫካው ተሰደው ያሉትን የኮንሶ ተወላጆች ታዲነው እንደሚገደሉ አስጠነቀቀ፡፡

In News, Standard by Konso People1 Comment

ባሳለፍነው ሳምንት የኮማንድ ፖስቱ አባላት ከየቀበሌዎች ከተውጣጡ የኮንሶ ተወካዮች ጋር ባደረጉት ውይይት የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ እንደማይመለከታቸውና በአሁኑ ወቅት የፈረሰውን የመንግስት መዋቅር ለማደራጀት እንጂ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ እንዳልሆነ፤ እንዲሁም በጥያቄው ምክንያት የተሰደዱትን የኮንሶ ተወላጆች በ አስቸኳይ ወደ ስራ እንዲመለሱ ካልሆኔ ማደኛ ወጥቶ ባሉበት እንዲገደሉ በሚል ዛቻና ማስፈራርያ ውይይቱ ተጠናቀዋል፡፡ ፡፡

ከኮንሶ በደረሰን መረጃ መሠረት በውይይቱ ወቅት ከህዝብ ተወካዮች መካከል 3 የሚሆኑ እንደታሰሩና ይህ በተደጋጋሚ እየሆነ እንዳለ፤ በተለይ ህዝቡ ውይይት ተብሎ እየወጣ ለእሰራትና ለእንገልት መዳረጉ ፤ በውይይቱ ወቅት የካዲረዎቹ አቅጣጫና ሃሳብ ብቻ በግድ ህዝቡ እንዲቀበል ማድረግና ከህዝብ የሚነሱ ጥያቀዎች ምንም ቦታ እንደለላቸው መታፈናቸው ህዝቡን በከፊተኛ ሁኔታ አማሯል፡፡

ይሄን አስመልክቶ በሁኔታው የተደናገጡ አንዳንድ ግለሰቦች በግደታ በኮማንዱ ፖስቱና የወረዳው ካቢነዎች የተዘጋጄ ፎርም ሞልተው በከፊተኛ ማስጠንቀቂያ ወደ ስራ እንዲመለሱ እንቅስቃሰ እየተደረገ ሲሆን በተለይ ህዝቡ የመረጣቸውን 23 ተወካዮች ወንጀለኛ ብለው ፈርጀዋል፡፡

በአሁን ሰዓት የኮንሶ ህዝብ በከፍተኛ አፈና ላይ ሲሆን ከአንድ አመት ተኩል በላይ ምንም አይነት የሚረባ ሚላሽ ለህዝቡ ሳይሰጥ በአፌሙዝ ህዝብን ደፍጥጦ የማሳመን ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

ህዝቡ የወከላቸው ግለሰቦች በአሁን ወቅት በከፊተኛ ሁኔታ እየታደኑ ሲሆን ላለፉት 2 ዓመታት በኮንሶ ካዲሬዎች የተፈጸሙ ጥፋቶችን ወደ እነሱ በማላከክና በተለያዩ የሀሰት ወንጀሎች ዘብጢያ ማውረድ ዋና አላማቸው ነው፡፡ ህዝቡ ግን በዝህ ጉዳይ ለድርድር እንደማይቀርብ ከወዲሁ አስታዉቋል፡፡

ከዝህ ጋር ተያይዞ በህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱና ህዝብን ለእንግሊት ያበቁ ጠቋሚ የኮንሶ ልጆች ከፊተኛ ህዝባዊ እርሚጃ እንደሚጠቢቃቸው ከተለያዩ የኮንሶ ቀበሌያት የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

View Post

በኮንሶ ግድያው ቀጥሏል ..

In News, Standard by Konso People1 Comment

እ.አ.አ December/ 9/ 2016 በተለያዩ የኮንሶ ቀበሌዎች በደቡብ ልዩ ሃይል ወታደሮች የተለያዩ ጥቃቶች ደርሰዋል፡፡

 1. ቡሶ እና ዶካቱ በሚባሉ የኮንሶ ቀበሌዎች ሴቶች የወታደሮች ጾታዊ ትንኮሳ ሰለባ ሆነዋል እንዲሁም በቁጥረ 2 የሚሆኑ ተደፍረዋል፡፡
 2. ደራ ቀበሌ ውስጥ የደቡብ ልዩ ሃይል ወታደሮች ባደረሱት ጥቃት የ12 ዓመት ታዳጊ እጁ ላይ በጥይት ተመቷል፡፡
 3. መጨሎ በሚባል ለላ ቀበሌ ውስጥ ደግሞ በተመሳሳይ ቀን የ60 ዓመት አዛውንት በጥይት ተገለዋል፡፡

በኮንሶ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አየተበራከተ ሲሆን በአሁን ሰዓት የኮንሶ ህዝብ ከፍተኛ ትኩረት ከ ሁሉም የህብረተሰብ  አባላት ይሻል፡፡

View Post

Petros Belachew ና Tadele Korano የሚሉ የFacebook አካውንቶች ከተጋለጡ በኋላ በ24 ሰዓታት ጠፉ(Delete)ተደረጉ፡፡

In News, Standard by Konso People1 Comment

አቶ ጰጥሮስ በላቸው ከአንድ አመት በላይ የኮንሶን ህዝብ ትግል ያንቋሸሸበትን ና Tadele Korano በሚል ስም የሚታወቀውን የፌስቡክ አካውንት ትላንት በኮንሶ ሚድያ ለህዝብ ይፋ ከወጣ በኋላ ዛሬ የግል አካውንቱን ጨምሮ አጥፍቷል፡፡

እስካሁን ፖስት ያደረጋቸውን አጸያፊና ቆሻሻ ቃላቶቹን ለመደበቅ አካውነቱን ቢያጠፋም ከህዝቡ ህልና የማይጠፋ እኩይ ተግባር እንደሆነ አውቆ ከዝህ ድርጊቱ ለወደፍት እንዲቆጠብና የበደለውን ህዝብ ይቅርታ በይፋ እንዲጠይቅ ያስፈልጋል፡፡

 

tadlekor

Tadele Korano የሚለውን የ ፈስቡክ አካወንት ስትከፍቱ ይሄን ያሳያል

Petros Belachew የሚለውን ዋና የፌስቡክ አድሻውን ሙሉ በሙሉ መረጃዎችንና ፎቶዎችን አጥፍቶ አካውንቱን ባዶ አድርጎታል፡፡

peterbel

ለማረጋገጥ ፈስቡክ ላይ ገብተው Petros Belachew ወይም Tadele Korano ብለው ይፈልጉ ..

 

View Post

Tadele Korano በሚል የውሸት የ Facebook አካውንት በኮንሶ ህዝብ እየቀለደ የነበረው ግለሰብ ታወቀ፡፡

In News, Standard by Konso People2 Comments

እ.እ.አ. ከ መይ 30/2015 ጀምሮ Tadele Korano በሚል የውሸት ፈስቡክ አካውንት አውጥቶ ብቅ ያለው ግለሰብ ከ ጊዜ ወደ ጊዜ ፖስት የሚያደርጋቸው የጽሁፍ መልክቶች የኮንሶን ህዝብ ህልውናን የሚጎዱና ፍፁም ከእውነት የራቁ ከመሆንም በላይ ህዝብ የመረጣቸውን 23 ተወካዮች መሳለቅያ አድረጓቸው ነበር፡፡ በተለይ የኮንሶን ህዝብ ጥያቄን በሚደግፉ ግለሰቦችም ላይ በግል የስም ማጥፋት ዘመቻ በተደጋጋሚ  አድርጓል፡፡ የዝህን ግለሰብ ጫፍ የወጣ ጥላቻ ከምን የመነጨ ይሆን በሚል ማንነቱን ለማወቅ በተደረገ ከፍተኛ ትግል ግለሰቡ Petros Belachew መሁኑ በተጨባጭ መረጃ ተረጋግጧል፡፡

ይህ ግለሰብ በትላንትናው እሌት Deember 6/2016 እንደለመደው የኮንሶ ሚድያን ቢያብጠለጥልም ከፅሁፉ ጋር ፖስት ያደረጋቸው ፎቶዎች ገመናውን አውጥተዋል፡፡

በታደሌ ኮራኖ ፈስቡክ ፖስት ላይ ይሄን ምስል download አድርጋችሁ  በፎቶው ላይ

15317750_1746568495666848_7662032279436609232_n-2

1. Right click

2. Properties

3. Details ላይ ክልክ ቢታደርጉ ባለበቱ(Author) Petros Belachew መሆኑነ ታረጋግጣላችሁ፡፡

እንዲሁም ታደለ ኮራኖ የሚል የፈስቡክ  አካውት ከወጣ ወድህ ግለሰቡ ሳያውቅ ፖስት በሚያደርጋቸው መረጃዎች የ IP Address trace ሲደረግ የ Petros Belachew ና የ Tadele Korano ከተመሳሳይ ስፍራ መሆኑ በተጨማሪ የሁለቱንም አካውነቶች ታርክ ሲጠና ሁለቱም ከተመሳሳይ አከባቢ መሆናቸው የግለሰቡን ማንነት ለማወቅ ቀላል አድርጎታል፡፡

tadko1

ታደለ ኮራኖ ብሎ እራሱን የሰየመው ጰጥሮስ በላቸው እ.አ.አ በ 24 October 2015 በደብሬ ብርሃን ነበረ፡፡ ከላይ የሚታዩትን ፖስት አድርጎ እራሱ መልሶ እንዳይታወቅበት ኮመንት ያደረገበት ና

petbel

በተመሳሳይ ሁኔታ Petros Belachew በሚል አካውነቱ ከዛው ከደብሬ ብርሃን ከተማ በ1ቀን ልዩነት ፖስት ማድረጉ ና ከ December 2015 ጀምሮ በአድስ አበባ እንዲሁም በየሄደበት ሁሉ ሁለቱን የተለያዩ አካውንቶች እያፈራረቀ መጠቀሙ በማስረጃ ተደርሶበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በህዝብ መሃል ሆነው ከፈስቡክ ጀርባ ተደብቀው በህዝብ ጥያቄ ና ሲቀይ የሚያሾፉ ብዙዎች አሉ፤ እነኝህ ግለሰቦች በአስቸኳይ ከዝህ እኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡና ከዝህ ወድህ በተለያየ ሁኔታ ከፍተኛ ክትትልና ለህዝቡ የማጋለጥ ሲራ እንደሚሰራ ከወድሁ እናሳውቃለን ፡፡

ሁሉም የኮንሶ ተወላጅ እነዝህን የህዝብ ጠላቶች  በከፍተኛ ሁኔታ እንዲታገላቸው የኮንሶ ህዝብ ከወዲሁ ጥሪዉን ያቀርባል፡፡

View Post

በኮንሶ ለብዙ ሺህዎች መታሰርና ሞት ምክንያት የሆኑ ጠቋሚዎች ስም ዝርዝር ወጣ፡፡

In News, Standard by Konso People1 Comment

ከኮንሶ ህዝብ የመዋቅር ጥያቄ ጋር ተያይዞ ላለፉት 15 ወራት የኮንሶ ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ የሰብአዊ መብት ጥሰት እየደረሰበት ይገኛል፡፡ ሆኖም ከሠላማዊ ጥያቄው ማግስት ጀምሮ በርካታ የኮንሶ ተወላጆች በእነዝህ ግለሰቦች ውንጀላና ጥቆማ ባልፈፀሙት ወንጀል ለከፍተኛ ድብደባና እስራት እንዲሁም ለሞት ተዳርገዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከ2000 (ሁለት ሺህ) በላይ የሚሆኑ ሠላማዊ የኮንሶ ተወላጆች በካራት ደረቅ ፖሊስ ጣቢያ ፤ በጊዶሌ ማረሚያ ቤት ፤ በአርባ ምንጭ ማርምያበት እንደሁም በካራት ከተማ የኢንዳስትሪያልና ተክንክ ኮሌጅ ባልፈፀሙት ወንጀል በእነዝህ ግለሰቦች ጥቆማ ብቻ ሲቃይ ላይ ይገኛሉ፡፡

የጠቋሚዎቹ ስም ዝርዝርና የስራ ድርሻ  በከፍል፤

 1. ያቨሎ ያላ (መንገድና ትራንሰፖርት ቢሮ ሠራተኛ)
 2. ዘመኑ ኦንጋየ (የሴቶችና ህፃናት ቢሮ ሠራተኛ)
 3. ገበየሁ ገማይዳ (መ/ር)
 4. አዲሱ ጉዮ (መ/ር)
 5. ኢዮብ ሰንቤቶ (ማይኮ ተብሎ የሚታወቅ የ ቀጠና 1 ነዋሪ)
 6. ፍትራሬ ገበየሁ( ዲኤ ግብርና ሠራተኛ )
 7. ሳሶ ቢሴ (ፖሊስ)
 8. ኦርካይዶ ኩቹሎ (ፖሊስ)
 9. ተስፋዬ ገለቦ (የፖሊስ አዛዥ)
 10. ለሚታ ፈረደ (የሻሺቱ ባል)
 11. በርሻ ካንሲቴ (ፖሊስ)
 12. ገዝሃኝ ኦዳ (የንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ሠራተኛ)
 13. ካንቢሮ አዘጋጅ (ፖሊስ)
 14. ኩሩጫ (ፖሊስ)
 15. ሳሙኤል ገለቦ (የፋይናንስ ኃላፊ)
 16. ካንሲቴ ዱባ (የዋና አስተዳዳሪ ፀኃፊ)
 17. ገረሙ ገንጮ (የፋይናንስ ሚ/ኃላፊ)
 18. በራቆ በናታ (የፋይናንስ ቢሮ ልማት እቅድ ሰራተኛ)
 19. ከበደ ጋዮላ (የፋይናንስ ግ/ፋ/ን ኃላፊ)
 20. ያቨሎ ኩሴ (የሠገን ዞን መ/ትራንስፖርት ኃላፊ)
 21. ኩሴ ካምቢሮ (የድርጅት ከተማ ዘርፍ ኃላፊ)
 22. ምስጋና ብርሃኔ (የበራቆ በላቸው /የቀድሞ አስተዳዳሪ ባሌበት)
 23. ከፊታ (የሞያሌ ነጋዴ)
 24. አለማየሁ አያኖ ዳኘ (የቀጠና አንድ ነዋሪ)
 25. አያኖ ዳኜ (መ/ር)
 26. ንጋቱ መንገሻ (አቡ ጠጄ)
 27. በየኔ ዮሰፍ (የካራት 2ኛ ዴ/ ር/መር)
 28. ታጋይ (የፋሻው ሞተረኛ)
 29. አሻኩሬ (የቱሪስት ጋይድ)

ከዝህ በላይ ስማቸው የተጠቀሰ ግለሰቦች በቀጥታም ሆኔ በተዘዋዋሪ የኮንሶ ህዝብ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱና የህዝብን ጥያቄ ለግል ጥቅማቸው ብለው ያፈኑና የከዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በ43ቱም የኮንሶ ቀበሌያት ከደቡብ ልዩ ሃይሎች ጋር በመሆን የኮንሶን ምሁራንንና ወጣቶችን በማሳደን ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዝህ እኩይ ተግባራቸው በአስቸኳይ ካልተመለሱ ህዝቡ ከፍተኛ የሆኔ እርምጃ እንደምወስድ ከወድሁ አስታውቋል፡፡

View Post

ኮንሶዎች በጅምላ እየታሰሩ ነው፤ ኢ-ሰብአዊ ድርግቱን የሚያስቆም ሰሚ አካል ጠፍቷል፡፡

In News, Standard by Konso People0 Comments

በልዩ ሁኔታ የኮንሶ ህዝብ ቅር መሰኘቱንም በተለየዩ ስብሰባዎች እና አጋጣሚዎች ገልጾአል፡፡ በጋራ መግባባት ላይ ያልተመሰረተ አሰራርን ተከትሎ በህዝቦች በመፈቃቀድ ላይ ብቻ የተመሰረተ የፖለቲካ ማህበረሰብን መገንባት መርህን ያልተከተለ ስህተትም ተሰርቷል፡፡ በዞኑ ምስረታ ወቅትም በክልሉ አመራር የልዩ ወረዳ መዋቅር ፈርሶ በክልሉ የሚገኙ ልዩ ወረዳዎች ወደ ሚቀርባቸው ዞኖች እንደሚቀላቀሉም ቃል ተገብቶ ነበር ግን ሌሎች ልዩ ወረዳዎች ላይ ተመሳሳይ አሰራር የተከተለ አካሄድ የለም፡፡
መጋቢት 2004 ሰገን ዞን ሲቋቋም የዞኑ ማዕከል ላይም ቢሆን የህዝቦች ምክክር ሳይደረግ የክልሉ አመራር በሰሜን ምስራቃዊ አቅጣጫ በኮንሶ ብሔር ክልል ውስጥ ሰገን ከተማ በሚትባል ቦታ እንዲቀመጥ አድርገዋል፡፡ በሰኔ 2004 የኮንሶ ህዝብ ሳይወስንና ሳይፈቅድ የዞኑ አመራር ባሳለፈው ውሳኔ ከኮንሶ ህዝብ ሶስት ቀበሌያት ማለትም በቾ፣ አዲስ ገበሬ እንዲሁም ሰገን ከተማ ወደ ከተማ ክልል እንድገቡ ውሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ ይህም ሉዓላዊ የኮንሶ ህዝብ ምክር ቤት ሳይወስን የተደረገ ስህተት ነው ማለት ነው።፡፡ ይህ በዚህ ሳይበቃ ከ2004 የዞኑ ምስረታ ጀምሮ የዞኑ ማዕከል ህጋዊ ድጋፍ እና ውሳኔ ከኮንሶ ምክር ቤት በኩል አለማግኘቱ እና እስከ አሁንም ድረስ ውሳኔ አለማግኘቱ ሌላው የዞኑና የክልሉ አመራር ህጋዊነት ያልተከተለ ስህተት ነው፡፡
የኮንሶ ህዝብ አብላጫ ከመሆኑ የተነሳ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅሞቼን ተነፍግያለሁ በማለት ጥያቄ እያነሳ ቢሆንም ምላሽ ሰጪ አካል በማጣት ከዞኑ ምስረታ ማግስት ጀምሮ ባለው መዋቅር ደስተኛ አይደለም፡፡ ለአብነትም ያህል:
➢ ፍትሀዊ የበጀት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርና እንድሁም ማህበራዊ ጥቅሞች መጓደል
➢ ብሄርን መሰረት በማድረግ ጥቃቶችን ማድረስ (ከኮንሶ አርባምንጭ በሚወስደው መንገድ የዞን አመራር አርሶ አደርን ያለምንም ምክንያት መግደል እና ተመጣጣኝ ቅጣት አለመቀጣት)፣
➢ ከዞኑ መንግስት መስሪያቤቶች የኮንሶን ብሄር ተወላጅ ማግለል
➢ ነባር አርሶ አደሮችን ከጎረበት ህዝቦች ጋር ማጋጨት ከመረት ማፈናቀልና ከሰው ክልል ውጡ በማለት በህዝቦች መካከል ቅራኔ ማባባስ (በኮልሜ፣ በቡርጂ እና በኦሮሚያ ባሉ አዋሳኞች)::
የኮንሶ ህዝብ ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ በዋናነት የተነሳው ከዚህ በላይ በተጠቀሱ እና ሌሎች ችግሮች ምክንያት ቢሆንም በ2004 ህጋዊ ውሳኔ ያላገኘ የከተማ መዋቅር፣ በኮንሶ ወረዳ ውስጥ ያሉ ቀበሌያት ወደ ከተማ ያለ ህዝብ ፈቃድ መከለል፣ ህዝቡ ቀድሞ በልዩ ወረዳነት ራስ-ገዝ በሆነ መዋቅር መተዳደር የተለማመደው የተሻለ፣ አንጻራዊ ልማት፣ እና በህዝቡ ላይ የደረሱ በደሎች ተደማምረው ለጥያቄው መንስኤ ሆኗል፡፡
በሐምሌ 2007 የዞኑ አመራር በኩል የከተማ መዋቅር ቀድሞ ውሳኔ ያገኘ በማስመሰል ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ ማድረግ የአመራሩ የህግ ጥሰትን አጉልቶ በማውጣት ከፍተኛ የህዝብ ንቅናቄ ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም:
➢ ተቃውሞው በሰፋፊ ህዝባዊ ሰልፎች በተለያዩ ጊዜያት ተደርጓል፡፡ በተለይም በአንድ ጊዜ ከ50,000 ህዝብ በላይ እየተሰበሰበ ታላላቅ ትዕይንቶች ከአራት ጊዜ በላይ ተደርገዋል፡፡
➢ ለፈደራል እና ለክልል ፈደረሽን ምክር ቤቶች እንድሁም ለሚመለከታቸው አስተዳደር አካላት በተደጋጋሚ ጥያቄው ቀርቦአል፡፡ ተገቢ ምላሽም አልተገኘም፡፡ የፈደራሉ እና የክልሉ ህገመንግስትን መሰረት ያደረገ ምላሽ ባለመሰጠቱ ህዝቡ አልረካም ምላሹንም እየተጠባበቀ ይገኛል፡፡ በተለይም የክልሉ መንግስት ህጋዊ ምላሽ የመስጠት ሃላፊነት ያለበት በመሆኑ ህዝቡ በትዕግስት ይጠባበቃል፡፡
➢ ህዝቡ አላምንባቸውም ያላቸውን የተወካዮች ምክር ቤት (አንድ ሰው) እንድሁም የክልል ምክር ቤት ተወካይ (አንድ ሰው) ይውረድልኝ በማለት ከ50000 በላይ ፊርማ በህዳር ወር 2008 ዓ.ም በማሰባሰብ ለፈደራል እና ክልል ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤቶች ገቢ አደርጎ እስካሁን አድርጎ ምላሽ አልተሰጠውም፡፡
➢ የኮንሶ ወረዳ ምክር ቤት በሙሉ ድምጽ የራስ በራስ የማስተዳደር እና በዞን የመዋቀርን ጥያቄ ማቅረብን እንድሁም ያለ ምክር ቤቱ እውቅና ከወረዳው ላይ የተቆረጡ ቀበሌያት ሙሉ በሙሉ እንድመለሱ፣ ህዝብ ያላመነባቸው አመራር አካላት ከህዝብ ሰልጣን እንድወርዱ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡
ይህ ሂደት ፍጹም ሰላማዊ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓትን ተከትሎ እየሄደ ያለ ቢሆንም አንዳንድ የዞን እና የክልል አመራር አካላት:
➢ ከህዳር ወር 2008 ጀምሮ የክልሉን ልዩ ሀይል ወደ ወረዳው በማሰማራት ድብደባ፣ ዘረፋ፣ እስራት እና የህዝብ ተቋማትን በመውረር ሰላማዊ አከባቢን ከማወክ በተጨማሪ ደበና በሚባል ቀበሌ ሁለት አርሶ አደሮችን በቀን 4/07/2008 በጥይት በመደብደብ ግድያ ፈጽመዋል፤
➢ ለሁሉም ወታደራዊ ጫና የኮንሶ ህዝብ የሰጠው ትዕግስት የተሞላበት አካሄድ እና ሰላማዊ ሂደትን የተከተለ በመሆኑ የክልሉ አመራር የበሰለ አመራር መስጠት አለመቻላቸው፤
➢ የህዝብ ጉዳይ እንድያስፈጽሙ የተመረጡትን 12 ግለሰቦች በማስፈራራት በህዳር ወር 2008 አርባ ምንጭ፣ በጊዶሌ ከወረዳቸው ውጪ በማሰር ማንገላታት፣ የተለያዩ የውሸት ወሬዎችን ማሰራጨት
➢ የኮንሶ ህዝብ ባህሉን አክብሮና ከመንግስት ጋር ላለፉት ጊዜያት በከፍተኛ ደረጃ በመግባባት ለልማት ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ ቢሆንም ለህዝቡ ጥያቄ ከተወከሉት ውስጥ ከባህል መሪዎች መካተታቸውን ለመከላከል ሲባል ብቻ ባህልን ማንቋሸሽ አልፎም ከ9ኙ የኮንሶ ጎሳ መሪዎች አንዱን በአርባ ምንጭ ማረሚያ ያለ ምክንያት ማሰርና መፍታት፣ የባህል ንብረቶችን ከጎሳ መሪ መግፈፍ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሶአል፤
➢ የህዝቡን ጥያቄ የግንቦት ሰባት፣ የጥቂት ሽፍቶች፣ የሰማያዊ ፓርቲ፣ የኦነግ፣ የተቃዋሚ ፓርቲ በማለት የህዝብን ህሊና መጉዳት (በተጨባጭ በአከባቢ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ማሰተላለፍ)፤
➢ የጥያቄው ህጋዊነት ላይ ታምኖ የፈደራል መንግስት ህዝቡ የወከላቸው 12 አባላት ከክልሉ መንግስት ጋር በመሆን የህዝቡ ጥያቄ በአግባቡ እንድፈታ አቅጣጫ የተቀመጠ ቢሆንም ክልሉ ጥያቄው እንድነሳ ፈጽሞ አለመፈለጉ ጉዳዩ እልባት እንዳያገኝ አድርጓል፤
➢ የህዝቡ ንቃተ ሂሊና እና የአላማ ጽናት ከዞኑ እና ከክልሉ አመራር በላይ በመሆኑ ለሚወሰዱ የሀይል እርምጃዎች ትዕግስት የተሞላበትና ሰላም የሰፈነበት ትግል ብቸኛና ትክክለኛ መስመር መከተል ህዝብን የሚያስመሰግን ነው፤
➢ ሕዝቡ የጠየቀውን ጥያቄ ምላሽ በጽሁፍ ከነምክንያት እንድገለጽለት የፈለገ ቢሆንም ምንም ዓይነት ምላሽ እስከ ሚያዝያ አጋማሽ ድረስ አለመሰጠት፤
➢ ከራስ በራስ የማስተዳደር ጥያቄ ጋር ብቻ በተያያዘ ከ250 በላይ ሰዎች ታስረው ያለምንም ምክንያት መለቀቅ በህዝቡ ዘንድ ቅራኔ ፈጥሯል፡፡ እስከ 17/8/2008 ድረስ አራት የኮንሶ ብሄር ተወላጆች ከወረዳው ውጪ በአጎራባች ወረዳ ከአራት ወራት በላይ እስራት ላይ ይገኛሉ::
የተጠየቀው ጥያቄ ህጋዊነቱን እና ህገመንግስታዊ አካሄዱን የጠበቀ እስከሆነ ድረስ ህጋዊ ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ይህ ጥያቄ ለምን ተጠየቀ ተብሎ የሀይል እርምጃ መውሰድ ዘላቂና ተገቢ መፍትሄ ፈጽሞ አይሆንም፡፡ የኣካባቢው አመራሮች እየፈፀሙት ያለው ወንጀል ልክ የለዉም። በሰሞኑ ግርግርም ወደ ሶስት መንደር እሚሆኑ የሳር ጎጆዎች መቃጠላቸዉና ነብሳቸው ለማዳን ሲሉም በርከት ያሉ ኮንሶዎች ለመሰደድ መገደዳቸው ለመረዳት ችያለሁ።
ፌዴራላዊና ሕገ መንግስታዊ ስርዓቱን ወደላቀ ደረጃ ሊያደርሱ እሚችሉ ዴሞክራስያዊ የህዝቦች ተሳትፎ ተገቢ ምላሽ እንጂ ዱላና ጠብ-መንጃ አይገባቸዉም። የክልሉና የፌዴራል መንግስትም ሁኔታው እጅግ አሳሳቢ መሆኑ ተገንዝበው አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጡ እማፀናለሁ።
ግልባጭ
➢ ለ ክቡር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስቴር
➢ ለ ኢፌዴሪ ፌዴሬሽን ምክር ቤት
➢ ለፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር
➢ ለኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክርቤት
➢ ለደቡብ ክልል መንግስት
➢ ለሁሉም የግል እና የመንግስት ሚድያዎች

ከሰላምታ ጋር!

አባ ሂሩት ባጫ ከኮንሶ ካራት
ጤና ይስጥልኝ!!!

View Post

የኮንሶ ማህበራዊ ድህሬ-ገጽ konsopeople.com በGoogle ከፍተኛ ደረጃ አገኘ፡፡

In Standard by Konso People2 Comments

የህዝብ ድምፅ የሆነው የኮንሶ ህዝብ ማህበራዊ ድህሬ-ገጽ ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሱ ያሉትን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ በደሎች በፍጥነት ወደ ህብረተሰቡ በቀጥታ እንድደርስ በሚል አላማ የተሰራ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በጎግል የፍለጋ ድህረ-ገፅ የመጀመርያ ገፅ ላይ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመታየት በቅቷል፡፡ ይህ ማለት፡ – ማነኛውም ሰው ከየትም ቦታ ሆኖ የጎግል ገጽ ላይ Konso  ወይም Konso People ብሎ ብጽፍ በቀጥታ የመጀመርያው ገፅ ላይ የድህሬ-ገጹን አድራሻ ያገኘዋል:: ይሄም የኮንሶ ህዝብን ድምፅ ተደራሽነት በእጅጉ ያልቀዋል ተብሎ ይጠበዋል፡፡

111

ሁሉም የኮንሶ ተወላጅ በአሁኑ ወቅት በህዝቡ ለይ እየደረሰ ያለውን ጫናና በደልን እንዲያወግዘውና በተቻለው መጠን መረጃዎችን በድህሬ-ገጹ  ላይ ሼር በማድረግ የበኩሉን እንዲወጣ በአክብሮት ተጋብዟል፡፡

ድል ለታሪክ ሠሪው ህዝብ!

View Post

በኮንሶ ቀበሌዎች የውሃ ጉድጓዶችና የእህል ወፍጮዎች በደቡብ ልዩ ሃይል ወታደሮች ተከበው አገልግሎት እንዳይሰጡ እየተደረገ ነው፡፡

In News, Standard by Konso People3 Comments

በዝህ ሳምንት የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ /ደኢህዴን/ የክልል ማዕከል
አመራሮች በጥልቀት የመታደስ የንቅናቄ መድረክ በሚል ባለ 9 ነጥብ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡

15107487_1341722722524835_2172140033729160678_n

በቁጥር 8(ስምነት) በክልላችንበጌዴኦ ዞን እና በኮንሶ ወረዳ በጸረ ሰላም ሀይሎች ግፊት በህዝባችን ውስጥ የተፈጠረው አይነት የፀጥታ ችግር ዳግም እንዳይከሰት እኛ አመራሮች አስቀድመን ሁኔታዎችን በመገምገም ለህዝብ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሾች እንዲሰጡ በማድረግም ይሁን ቀደም ብለው በተፈጠሩ ክስተቶች ለተጎዱ የህብረሰብ ክፍሎች ከህዝባችን ጎን በመሆን ተገቢውን ማቋቋሚያ ድጋፍ በመስጠት የመሪነት ሚናችንን ለመወጣት ዝግጁዎች መሆናችንን እናረጋግጣለን፡፡

የሚል ቢሆንም በተጨባጭ በኮንሶ ቀበለዎችና መላው ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ጫናና በደል በእጥፍ እየጨመረ ይገኛል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ህዝቡ መሰረታዊ አገልግሎቶችን እንዳያገኝ በተለይ የውሃ ድጓድ (ኤላ) ኮንሶዎች ለብዙ ሺህ አመታት በራሳቸው የተፈጥሮ ሳይንስ ቆፍረው የሚጠቀሙበትን የውሃ ምንጮች በወታደሮች ተከበው አገልግሎት እንዳይሰጡ ሲደረግ ለመጀመርያ ግዜ ነው፡፡ እንድሁም በየቀበለዎች ውስጥ የሚገኙ የእህል ወፍጮ ማሽን በቶች እንዲዘጉ መደረጉ የኮንሶን ህዝብ ቁጣና እምቢተኝነትን ከማባባስ በቀር ፋይዳ እንደለለው ህዝቡ በተደጋጋሚ ከስፍራው እየገለጸ ይገኛል፡፡ ይህ ድርግት የአንዳንድ ጠባብ ፓለትከኞች እኩይ ተግባር መሆኑ ግልፅ ቢሆንም የፌደራል መንግስት በኮንሶ ህዝብ ላይ የተቃጣውን ዘመቻ እስከታች ወርዶ ችግሩን እንዲያጣራና ወንጀል ፈፃሚ የመንግስት ባለስልጣናት በህዝብና መንግስት መካከል ለፈጠሩት ክፍተትና ውድመት ተመጣጣኝ እርምጃ እንዲወሰድባቸው የኮንሶ ህዝብ በአጽኖት ይጠይቃል፡፡

ከታታሪው የኮንሶ ህዝብ!

View Post

በኮንሶ ታፍነው የታሰሩ ሰዎች ቁጥር ከ 1000 (አንድ ሺህ) መብለጡ ተነገረ፡፡

In News by Konso People1 Comment

ኮንሶ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ ቀበሌዎች እና ካራት ከተማ በደቡብ ክልል ልዮ ሀይሎች አማካይነት በርካታ ሰዎች ወደ ማሰቃያ ሥፍራዎች እየተወሰዱ ሲሆን በየቀኑ ታፍኖ የሚወሰድ ሰው ቢዛት ቁጥር 40ና ከዝያ በላይ ደርሰሷል፡፡ በቀን 6/3/2009 ዓ.ም የህዝብ ተወካይ አባላት፡ ለአብነት በካራት ከተማ ብቻ:-
የመ/ር ገመቹ ገንፌ ባለቤት ፤
የአበል ለሚታ ባለቤት ፤
የመ/ር ጉዮ ጅሎ ባለቤት፤
የኦርኪሳ ኦራኖ ሴት ልጅ ናየሞጮራ ኦዳ ባለቤትና ልጅ… ሲሆኑ በተመሳሳይ ሰዓት በዶካቱ በሚባል ቀበሌ ብዙ ቤቶችን ሰባብረው እየገቡ ሰዎችን በመደብደብ 23 (ሃያ ሶስቱ) የህዝብ ተወካዮች ያሉበትን ቦታ ካልነገራችሁን በማለት ወደ ማሰቃያ ቦታዎች ወስዷቸዋል፡፡
እስከ ዛሬ ድረስ ከ1000 የሚበልጡ ያለ ወንጀል በተለያዩ ሥፍራዎች የታሰሩ
1. በካራት ፖሊስ ጣቢያ (ወደ አርባምንጭ በምወስደው መንገድ በስተቀኝ ያለ)
2. በካራት አንዳስቲርያልና ተክንክ ኮሌጅ (የድሮው አውራ ጉዳና ካምፕ አጠገብ)
3. በጊዶሌ ማረምያ ቤት
4. በአርባምንጭ ማረምያበት
ኢሰብአዊ በሆነ ሁኔታ ጧት ማታ የሚያሰቃዮ የኮንሶ ተወላጆች እንዳሉ ነዉ፡፡
ይህ ድርግት በኮንሶ ብሄር ላይ ያነጣጠረ እኩይ ተግባር ሲሆን መንግስት በፍጥነት የህዝቡን ጥያቄ በመመለስና ክራይ ሰብሳቢ ባለስልጣናትን አስወግዶ የኮንሶ ህዝብ ሠላምን እንድያረጋግጥ እንጠይቃለን፡፡

ከታታሪው የኮንሶ ህዝብ!

View Post

ኮንሶ ታላቅ ሰው አጣች! ዶ/ር አንቶ አርካቶ

In News by Konso People3 Comments

ይህ አመት ለኮንሶ ህዝብ የከበደው ይመስላል፡- ዶ/ር አንቶ ኮንሶ ካፈራቻቸው ግንባር ቀደም ምሁራኖች መካከል አንዱ ሲሁኑ በዛሬው ቀን እ.አ.አ. ኖቨንበር 16/ 2016 በድንገተኛ የመኪና አደጋ ህይወታቸው ማለፉ መላው የኮንሶ ህዝብ በጥልቅ ሃዘን እንዲዋጥ አድርጎታል፡፡  ዶ/ር አንቶ አርካቶ ለብዙ ታላላቅ የኮንሶ ልጆች ሚሳሌ የነበሩ እንዲሁም በሙያቸው ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳደሩ ከፍተኛ ሚሁርም ነበሩ፡፡ በአርባምንጭ ዩኒቨረሲቲ የድህረ – ሚረቃ ክፍል ዳይረክተር የነበሩት እኝሁ ታላቅ ሰው ከ ኔዘርላንድስ ቲወነተ ዩኒቨረሲቲ በትም/ት ካሪኩለም ቀረጻ የማስተረትና ዶክትረት ዲግሪ ማግኘታቸው ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም አፋ ኾንሶ በኮንሶ አከባቢ የትም/ት ካርከለም ውስጥ እንዲካተት ከፍተኛ ምርምር አድርገው ወደ ስራ ከመግባቱ በፍት ህይወታቸው ማለፉ ሃዘኑን መራር ያደርገዋል፡፡

15003381_1270959302966688_6535150158078449306_o

Dr. Anto Defending PhD dissertation in Twente University, Netherlands 11/12/2014

መላው የኮንሶ ህዝብ ለእኝህ ታላቅ ሰው ህይወት ማለፍ የተሰማውን መራር ሃዘን በተለያዩ የማህበራዊ ድህሬገጾች እየገለፀ ይገኛል!

መፅናናትን ለወዳጅ ዘመዶች እየተመኘን ከተለያዩ የኮንሶ ተወላጆች የቀረበ የሃዘን መግለጫ ከዝህ በታች እናቀርባለን …

በፈስቡክ ሃዘናቸውን ከገለጹ መካከል በጥቂቱ …

Gubae Gundarta feeling heartbroken.

Today, I woke up to the tragic news of the sudden and untimely passing of my friend, teacher, mentor, and role model Dr. Anto Arkato of Arba Minch University. I had to pinch myself to make sure that I wasn’t dreaming. …and I wish I was. His passion for education was rather infectious. He’s such an irreplaceable gem and a stellar intellectual who many of us who were lucky to have been taught by him had always looked up to. Though his sudden passing has torn our hearts out, the work he’s done shall live on in our memory. May his soul rest in peace! And we need to do something about car accidents which have continued to claim thousands of precious lives in the country every year. I really don’t know how many more lives we should lose before putting a stop to this as a nation. It is totally insane!

Kusse Koirita added 2 new photos — feeling shocked.

Feeling heartbroken about the accidental death of Dr Anto Arkato by a car accident.We lost an outstanding young scholar.
Dr Anto Arkato had been a lecturer at Arba minch university since 2000 and had also been serving as the director of school of graduate studies for the past three years.He obtained his MA and PhD from university of Twente in Netherlands.We all love you and miss you Dr Anto Arkato,you are a role model for all!
MAY YOUR SOUL REST IN PEACE!! OUR CONDOLENCES GOES TO HIS FAMILY AND BELOVED ONES

Yavello Nataye Yatasa feeling heartbroken with Anto Arkatoand Ongaye Oda Orkaydo.

Helsinki, Finland ·

You will be always remembered!!

I just learned that #Dr_Anto_Arkato will no more be with us. What a heart breaking news!! I don’t know what to say. An immeasurable loss for #Xonsitta, for his institution, #Arba_Minch_University and for our nation #Ethiopia. We lost a scholar, a teacher, a father and above all a role model. My condolences to his family, friends, colleagues and the whole Xonsitta.

34499_405798466174_578856_n

Dr. Anto with Dr. Onagaye in Netherlands, July 4, 2010

Tadele Orbula feeling sad. Cachan, France ·

I am very saddened to hear the loss of Dr. Anto Arkato. He was among the hard working and most respected people that I know. I would like to express my sincere condolences to his family. RIP.

Lukas Beyashe shared Kusse Koirita‘s post to the group: Xonso Ambassadors
RIP – my role model of hard work, previous colleague, advisor, big brother…… I am really heart broken.
feeling heartbroken.
Tatasha Takaye Kasito feeling heartbroken.
 RIP! What unfortune sunday is it!! We lost an invaluable asset in Dr. Anto Arkato that we would otherwise use for the new history building with new generation of Xonso. All sad story for all xonso people. Irreplceable loss, unable to control my emotion, Dr. Anto, you would be remembered always in our heart, RIP

Kasaye Soka feeling sad.

Please people around Arbaminch and Konso call and confirm the sad news that Dr. Anto Arkato has passed away by car accident. Please??

Kusse K. Bekele‎ to xonso ke fani

We have lost the Giants of our land!

It is with great sadness and sorrow that we’ve heard the death of Dr. AntoArxato (PhD) in a tragic car accident today. We have lost the giants of our time and a great son of ours who have worked tirelessly and passionately on education his whole life. His death has sent chills of anguish through our intellectual community and society at large. we have suffered an immeasurable loss, endless pain and distress as a community.

Some of us are still distraught, some of us are scratching our heads in disbelieve and those who can are screaming with a loud and cracking voices. we all are trapped in a moment of silence to reconcile within ourselves and accept reality. The light has gone out in our land and the darkness has overshadowed our family of community. Words may not suffice to express the heartfelt sorrow that we all feel, but we are deeply pained to the core of our humanity. He is great son of ours, a father figure to many, a mentor to his students, educator and a standard bearer of our society.

We cannot believe and we refuse to believe for that matter that you are no longer with us.We seek God’s mercy and forgiveness so that you might rest in peace and comfort to your children and parents.
Let us pay pious homage to this great son of ours, honor his work and remembrances to this gentle soul!

May You Rest in Peace!

Thomas T. Minda feeling pained with Anto Arkato.

It is hard to believe to me your passing away, Dr. Anto! It showed me that the best personality of human can be hopeless! It would have better to me not to known you. I’m feeling pained! I haven’t seen a person loved by all, but you! Beyond your range of academic capability, gifted & well-trained teacher, hard worker, high-level leadership quality, your pure heart amazes me. You served humanity irrespective of any class. It is also hard to me to forget you did for me! I lost my true friend! RIP, Dr Anto!

Blackbee Berisha

It is our sorrow for loss of Dr Anto Arkato (icon of hard work, rational humanity, respective, real teacher,………)
; rest in peace. I would like to express my condolences to his family and beloved. RIP!

Sika Shibru

It was unbelievable for what was happened. We didn’t able to control our tear because we Konso, AMU & all Ethiopians really lose a great person Dr Anto!RIP

Yonas Robayo

R.I.P! Feeling Sad! For Accidental Death Of Dr. Anto Arkato Ethiopia, Konso Losts A Great Man Of People Who Shows His Nations Meaning Of Phrase”the Icon Of Hard Working” Real Model For All! Dr. Anto Your Acts Always Live With As For Ever See You At Heaven!

Robisha Kusse

እይይይይይ የኮንሶ ልጅ Dr Anto Arikato !!!!!?????my heart is break!!!

Kachawa Lamita
 አዝናለሁ በአባታችን በዶ/ር አንቶ አርካቶ ድንገተኛ መለየት::

RIP

Mooha Xonso to xonso ke fani

ዶክተር አንቶ አርጋቶ !!!!!!!!! የደቡብ እትዮጵያ ታላቅ ምሁር፣ ለኮንሶ ህዝብ መብት በፅናት የምታገሉ፣ አስተዋይ፣ለህብረተሰቡ ተቆርቋሪ፣ትሁት፣አስተዋይ፣ቅንና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በእኩል አይን የሚያዩ ዛሬ በደረሰባቸው መክና አደጋ ህይወታቸው በማለፉ ጥልቅ ሀዘን የተሰማን መሆኑን እየገለፅን ለቤተሰቦቻቸው፣ለአርባምንጭ ዩኒቬርስቲ መምህራን፣ ተማሪዎችና ሰራተኞች፣ ለመላው ኮንሶ ህዝብና ለመላው ወዳጆቹ መፅናናትን እንመኛለን።

View Post

በግዳጅ ህዝቡን እንዲያሳምኑ በኮንሶ ምሁራን ላይ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገነው ተባለ

In News by Konso People1 Comment

1

ባሳለፍነው ሳምንት የተለያዩ በደሎች የኮንሶ ህዝብ ላይ ከመድረሱ በተጨማሪ ከህዝብ ጋር የሆኑ ምሁራንና የመንግስት ሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና በእጥፍ ጨምሯል፡፡ በተለይ የህዘብን ጥያቄ በመደገፍ የሚታወቁትና በትራፍክ ፖሊስነት ለብዙ አመታት ያገለገሉ አቶ ገመዳ ሮፓ ባልታወቀ ሁኔታ ሰገን አከባቢ ባለ እርሻቸው ላይ መገደላቸው የኮንሶን ህዝብ በጣም አስቆጥቷል፡፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰና እየጨመረ ያለው የመብት ጥሰትና ግድያ የኮንሶን ህዝብ በእጅጉ ያማረረ ሲሆን በአሁን ወቅት በካራት ከተማ ላይ ህዝብ የኛ ገዥ ነው የሚልና የተለያዩ የውሸት ፖስተሮችንና ባነሮችን በመለጠፍ ህዝብን የማታለል ስራ ቢሞክሩም ህዝቡ እሰከ አሁን ድረስ በተግባር ያየው ለውጥ ስለ ለሌና ጆሮው ለውሸት ፕሮፖጋንዳ ድፍን መሆኑን እየገለጸ ይገኛል፡፡

በአሁን ወቅት ግን ስልታቸውን ቀይረው በተለያዩ ቦታ በሙያቸው እያገለገሉ ያሉ የኮንሶ ምሁራንን በግድ አስመጥተው ወደ ህዝብ ገብተው እንዲያሳምኑ ከፍተኛ ጫና አያደረጉ ይገኛሉ፡፡ ይሁንና ማነኛውም የኮንሶ ምሁር በዝህ ጉዳይ በግደታ ሊጠራና ሊገደድ ስለምችል በተቻለ ሁኔታ ጥንቃቄ ቢደረግ እንዲሁም በምንም አይነት ሁኔታ ወታደር ይዞ ህዝብን ለማሳመን ሙከራ እንዳያደርግ ከወድሁ የኮንሶ ህዝብ ያሳስባል፡፡

የኮንሶ ህዝብ መሠረታዊ የሆኑ ጥያቄዎቹ ካልተመለሱለት በቀር በምንም አይነት መንገድ ለድርድር እንደማይቀርብ  በአንድ አቋም ገልጾአል፡፡

View Post

የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን እንደፈረሰ ተሰማ

In News by Konso People2 Comments

ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ አከባቢ ከፈደራል መንግስት ከፍተኛ አመራር በአርባምንጭ  በተደረገ ስብሰባ ላይ የሰገን አከባቢ ህዝቦች ዞን እንዲበተንና ወረዳዎቹ ወዴየቀደሞ መዋቅራቸው (ልዩ ወረዳ) እንድመለሱ ተደርጓል የሚል ጭምጭምታ በከፍተኛ ሁነታ እየተሰራጨ ይገኛል፡፡

ይህ ዜና ለኮንሶ ህዝብ ከፍተኛ ድል መሆኑን ጭምር በስፍራው የሚገኙ ነዋርዎች ገልፀዋል፡፡

እሰከአሁን ድረስ የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም ይህ ዜና ለህዝቡ እፎይታን እንደፈጠረ ከስፈራው የደረሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

ማሳሰቢያ

በ October 7, 2016 በአቶ ገመቹ ገሸርቶ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ድብደባ ህይወቱ እንዳለፈች ዘግበን ነበር፡፡ እንዲሁም ያለውን ሁኔታ ተከታትለን በስፋት መረጃውን ወደ እናንተ  አናደርሳልን! ብለን ነበር ፡፡ በጊዜው በአቶ ገመቹ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ድብደባ የተነሳ እራሱን ስቶ ስለነበረ በድንጋጠ ህይወቱ እንዳለፈ መረጃ ስለደረሰን ነበር አሁን ባጣራነው መሠረት ህይወቱ እነዳላለፈችና በከፍተኛ ሰቃይ ውስጥ እንዳለ ነው፡፡

View Post

ከ23ቱ የኮንሶ ተወካዮች አንዱ የሆኑት አቶ ገመቹ ገሻርቶ በደቡብ ልዩ ሃይል በኮንሶ እስር ቤት መገዴላቸው ተሰማ፡፡

In News by Konso People0 Comments

አቶ ገመቹ ገሻርቶ ከአድስ አበባ ዩኒቨሲቲ በፖለቲካል ሳይንስ የመጀመርያ ድግሪ ያገኙ ሲሆን በኮንሶ ህዝብ ተመርጠው እያገለገሉ ባሉበት በአሁኑ ወቅት በሰገን ዞንና ደቡብ ልዩ ኃይል ወታደሮች ከፍተኛ ድብደባ ከደረሰባቸው በኋላ ህይወታቸው ማለፉን ከኮንሶ የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

ያለውን ሁኔታ ተከታትለን በስፋት መረጃውን ወደ እናንተ  አናደርሳልን!

View Post

የኮንሶ ባህላዊ መሪ ካላ ገዛሃኝና በህዝብ የተመረጡ አባላት ታሠሩ

In Standard by Konso People0 Comments

በቀን 26/01/2009 ዓ.ም አድስ አበባ ከኮንሶ ተወካዮች ሁለቱን ካላ ገዛሃኝን እና አዳኔ ዝናቡን በኮንሶ ጉዳይ ላይ እንወያያለን ብለዉ ስብሰባ ጠርተዉ ጨርሰዉ ሲወጡ በዚያዉ አፍነው አስረዋል፡፡

23ቱ በኮንሶ ህዝብ የተመረጡ ተወካዮች እሰካሁን በስደት ላይ ናቸው፡፡ የደቡብ ክልል መንግስትና የሰገን ዞን ልዩ ሃይል ወታሮች እነዝህን ሰዎች ለመያዝ ሌት-ከቀን እየሰሩ ናቸው፡ ነገር ግን በህዝቡ ከፍተኛ ጥበቃ እስካሁን ማግኘት አልቻሉም፡፡

አሁንም ከ ኮንሶ ክልል ውጪ ያሉ ተወካዮችን አድነው በመያዝ ወደ ከርቸለ እየወሰዱአቸው ነው፡፡

እነኝህ አዕምሮ ቢስ አመራሮች ህዝቡን ከመቅረብ ይልቅ አሁንም የ ኃይል አማራጭ ተጠቅመው ህዝቡን የበለጠ ለማስቆጣት እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ ሲለሆነም  የታሰሩት ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱና በኮንሶ ምሁራንና አርሶአደሮች እንድሁም ወጣቶች ላይ የሚደርስ በደልና ማሳደድ ይቁም እንላለን፡፡

View Post

እስካሁን ድረስ በእስር ቤት እየተሰቃዩ ያሉ በኮንሶ ያለ ምንም ክስ ታፍነው የታሰሩ የኮንሶ ተወላጆች ከ ብዙዎቹ በጥቂቱ

In News, Standard by Konso People1 Comment

በርካታ የኮንሶ ተወላጆች  ታፍሰው ተወስደው አርባ ምንጭ ፖሊስ ጣቢያ ታጉረዋል፡፡ ሌሎችም በካራትና ግዶሌ ማረምያ በቶች

እንድሁም በማንም ሰብዓዊ ፍጡር ላይ ሊፈጸሙ የማይገባቸው ዕርምጃዎች በኮንሶ ሕዝብ ላይ እየተወሰደ ይገኛል፡፡

ከ300 በላይ የሚቆጠሩ የኮንሶ ወጣቶችና ምሁራን በተለያዩ እስር በቶች ታጉረው ይገኛሉ፤ እነሆ ከብዙዎቹ በጥቅቱ….

 1. ከፈኔ ትጫሮ (የኮንሶ ልማት ማህበር ኃላፊ)
 2. ገረሙ አያኖ(ትንሹ) ነጋዴ
 3. ለሚታ ጫሌ (ከደባና ቀበሌ ከምሽቱ 6፡00 ታፍኖ የተወሰደ)
 4. ኩሴ ካውደ
 5. አብነት ያቨሎ
 6. ካሮ ካሉሳ
 7. ገዝሐኝ ገለቦ
 8. ገብሬ ገዝሐኝ
 9. ከበደ ገዝሐኝ
 10. በለጠ ኃይሌ (መካኒክ)
 11. ምህረት ጎዳና (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 12. ሳጎያ ዋጨ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 13. ያቨሎ ጭራቶ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 14. ገዝሐኝ ጭራቶ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 15. አሊ ጭሀቶ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 16. ስሞን ካውዴ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 17. ኦልተ ኦቶማ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 18. አስመራ ደነቦ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 19. ጋሻው ሮብሻ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 20. ብርሃኑ በርሻ (ጎይቶም)
 21. በረከት ሮብሻ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 22. ጋሜ ገደኖ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 23. ነብዩ ሮብሻ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 24. መንግስቱ ሙሉ (የግርን ሆቴል ባለቤት) ነጋዴ
 25. ወንዱ ሮባ (የካራት ከተማ ነዋሪ)
 26. አድሱ ሙሉ (ነጋዴ) ዶካቱ ቀበሌ
 27. ሮብሻ ባዩ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 28. ሳጅን ገልቶ
 29. ሮቾ አይላቴ (የካራት ድስትርክት ሆሲፒታል ሠራተኛ)
 30. ኩሴ ኩርታይሌ (የመንግስት ሠራተኛ)
 31. ሳሙኤል በርሻ (የካራት ከተማ ነዋሪ)
 32. ደሣለኝ ካንቢሮ
 33. ጮልታ ጉደኖ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 34. ሸዋ ለሚታ
 35. ፍሬው ማሱላ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 36. ተስፋየ ጋማይታ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 37. ካሮ ግለዴ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 38. ገለቦ ኦራኖ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 39. ኩሴ ገለቦ ኛኛ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 40. ኩሴ ፍሬው (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 41. እርዳቶ ኦርካይዶ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 42. ዳዲ ፍሬው (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 43. ኩሴ ገሉቴ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 44. ኩማቾ ኩሴ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 45. ገልገሎ ጉዳና (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 46. ገለቦ አንኮኖ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 47. በያሼ ገለቦ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 48. ሐሞሽ ኩሲታ (የዱራይቴ ቀበሌ ነዋሪ)
 49. ታፈሴ ታምሩ
 50. ፍሬው እሸቱ (የካራት ከተማ ነዋሪ)
View Post

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ህገ መንግስታዊ መሠረት ያለውና ተገቢ መሆኑን የህግ ተመራማሪዎችና ከፍተኛ ምሁራን አስታወቁ

In News by Konso People2 Comments

ባሳለፍነው ሳምንት በተለያዩ የዓለም አቀፍ ዩኒቨረሲቲዎችና  በሀገር ውስጥ የህግ ተቋማት የሚሰሩ ከፍተኛ የህግ ተመራማሪዎች የኮንሶን ህዝብ ጥያቄ በጥልቀት መርምረው ሙያዊ አስተያየታቸውን ሰተዋል፡፡ ዶቼ ቨለ (የጀርመን ድምፅ ራድዮ) በቀን 15/01/09 ዓ.ም የኮንሶ ጥያቄ ግጭት እና መፍትሄው በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የዉይይት መድረክ ላይ ዶ/ር ፀጋዬ አራርሳ (የመልበርን የኒቨረሲቲ የህግ ተመራማሪ) ያለዉን ተጨባጭ  ሁኔታና የመፍትሄ አቅጣጫ ነው ያሉትን በዝርዝር ለሚድያው አስቀምጠዋል፡፡

በተጨማርም ሪፖርተር ጋዜጣ ርዕሱ የኮንሶ ብሔረሰብ የዞን ምሥረታ ጥያቄ ከሕግ አንፃር ሲፈተሸ በሚል በቀን 14/01/09 ለንባብ ካበቃው እትሙ ላይ በውብሸት ሙላት የቀረበ ሰፋ ያለ ማብራርያን እንዲሁም መንግስት ችግሩን በምን መልኩ መፍታት እንዳለበትና ለህገ መንግስታዊ ጥያቄ ህገ መንግስታዊ መልስ እንዲሰጥ ጭምር አሳስበመዋል፡፡

በተለይም ደግሞ ኮሎኔል አስጨናቂ /ጻዲቅ ሺፈራዉ  የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል ! በምል ርዕስ http://hornaffairs.com/ በተባለ ድግረ ገፅ በደቡብ ክልል ባለስልጣናት ላይ ከፍተኛ ትችት ሰንዝረዋል፡፡

ሙሉ መረጃ ከድህሬ ገፁ ይመልከቱ፡

የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ ተገቢዉን ምላሽ ይሻል !

 

ከሪፖርተር ጋዜጣ የተቀዳ ሙሉ ዘገባው ከዝህ በታች ተያይዞ ይቀርባል፡፡

 የኮንሶ ብሔረሰብ የዞን ምሥረታ ጥያቄ ከሕግ አንፃር ሲፈተሸ

በውብሸት ሙላት

ኮንሶ፣ በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በሰገን ሕዝቦች ዞን ውስጥ የምትገኝ ወረዳ ናት፡፡ ቀደም ሲል ግን ልዩ ወረዳ ነበረች፡፡ ኮንሶ አስተዳደር እርከን ብቻ አይደለችም፤ ብሔረሰብም ጭምር እንጂ! የሰገን ሕዝቦች ዞን ደግሞ በፊት የኮንሶ፣ የደራሼ፣ የአማሮና የቡርጂ ልዩ ወረዳዎች የነበሩትን በማጠቃለል የተመሠረተ ነው፡፡

በደቡብ ክልል ሕገ መንግሥት መሠረት ልዩ ወረዳ ከዞን ጋር አቻ ሥልጣን አለው፡፡ ተጠሪነቱም ቀጥታ ለክልሉ ነው፡፡ ልዩ ወረዳ፣ ብዙ ጊዜ በአንድ ብሔር ብቻ ስለሚመሠረት የአንድ ብሔር ብቻ አባላት ያሉበት የወረዳ ምክር ቤት ይኖረዋል፡፡ የራሱ የልዩ ወረዳው የሥራ ቋንቋ እንዲኖረው መወሰን ይችላል፡፡ በዞን ደረጃ የሚኖሩትን መንግሥታዊ መዋቅሮችን በወረዳው በማቋቋም በርካታ የብሔረሰቡ ተወላጆች የሥራ ዕድል እንዲኖራቸው ያስችላል፡፡

መደበኛ ዞኖች ሕግ አውጪ የላቸውም፡፡ የዞን ሥራ አስፈጻሚዎችም የሚሾሙት በቀጥታ በክልሉ ሥራ አስፈጻሚ በመሆኑ የክልል ውክልና እንጂ በምርጫ የተገኘ ሥልጣን አይደለም፡፡ ወረዳዎችም ቢሆኑ ለአስተዳደር ቅልጥፍና፣ ድጋፍና ክትትል ሲባል በተጨማሪነት ለዞን ተጠሪነት ያለባቸው ቢሆንም ይህ ሁኔታ የመነጨው የክልሉ አስፈጻሚ አካላት በሚሰጠው ውክልና ላይ ተመሥርቶ እንጂ ሕገ መንግሥታዊ መነሻ የለውም፡፡ ለዚያም ነው የወረዳ አስተዳዳሪዎችና ከንቲባዎች በዞን አስተዳዳሪዎች የማይሾሙትም ሆነ የማይወርዱት፡፡

በልዩ ዞኖች ግን የብሔረሰብ ምክር ቤት ስላላቸው፣ የዳኝነት መዋቅርና ሹመት በክልል ደረጃ ቢከናወንም እንኳን ከዞኑ የሚጠቆሙትና የሚሾሙት ዳኞች ላይ አስተያየት የመስጠት መብት አላቸው፡፡

የኮንሶ ብሔረሰብ፣ የዞንነት ጥያቄ በማንሳት ተቃውሞ ከጀመረ አንድ ዓመት አለፈው፡፡ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ ቀላል የማይባል የሰው ሕይወት ጠፍቷል፡፡ የክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ በቅርቡ በተናገሩት መረጃ እንኳን ከ1,500 ቤቶች በላይ ተቃጥለዋል፡፡ ከአንዳንድ መገናኛ ብዙኃን እንደሚሰማው የዞንነት ጥያቄው ካልተሳካ ወደ ኦሮሚያ ክልል የመካለል ጥያቄንም በአማራጭነት ሕዝቡ እያነሳ ነው፡፡ ይህ ጽሑፍ ዞን የሚመሠረትበትን ሕጋዊ አሠራር ይፈትሻል፡፡ የራስን ዕድል በራስ ከመወሰን መብት ጋር የሚኖረውን ግንኙነት በማየት የኮንሶ ብሔረሰብ ጥያቄ ከክልሉና ከፌዴራሉ ሕገ መንግሥት እንዲሁም ከሌሎች አግባብነት ካላቸው ሕጎች አንፃር ዳሰሳ ያደርጋል፡፡ እግረ መንገዱንም አንድ ወረዳ ወይንም ሌላ አስተዳደራዊ መዋቅር ከአንድ ክልል ወደ ሌላ ክልል መጠቃለል የሚችልበትን ሕገ መንግሥታዊ ሁኔታም ካለ ምጥን ፍተሻ ያደርጋል፡፡

ኮንሶ ከሌሎች ዞኖች ጋር በሕዝብ ብዛት ስትነጻጸር

የኮንሶን የዞን ምሥረታ ጥያቄን በአግባቡ ለመረዳት በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ዞኖች ጋር በ1999 ዓ.ም. የተደረገውን የሕዝብና ቤት ቆጠራን መሠረት በማድረግ  እናነጻጽራለን፡፡ በዚህ የሕዝብና ቤት ቆጠራ ውጤት መሠረት የኮንሶ ልዩ ወረዳ ወደ 235 ሺሕ የሚጠጋ ሕዝብ ነበረው፡፡ የዛሬ አሥር ዓመት የነበረው የወረዳው ሕዝብ ብዛት ማለት ነው፡፡ ከወረዳው ውጭም የሚኖሩትን ጨምሮ፣ የኮንሶ ብሔረሰብ ብዛት ከ250 ሺሕ በላይ ነው፡፡ ዞን ለመመሥረት በአንድ አካባቢ መኖርን ስለሚጠይቅ ለዞን ምሥረታ ጥያቄው ተገቢው ቁጥር መኖር ቅድመ ሁኔታ ነው ማለት ይቻላል፡፡

የኮንሶ ወረዳ ሕዝብ፣ ከሐረሪ ክልል ሕዝብ ይበልጣል፡፡ የዛሬ አሥር ዓመት የክልሉ ሕዝብ ብዛት፣ ገና 200 ሺሕ እንኳን አልሞላም ነበር፡፡ የኮንሶ ወረዳ በሕዝብ ብዛት፣ ከትግራይ ክልል የመቀሌ ልዩ ዞንን፣ ከአፋር ክልል የዞን ሦስትና አምስትን፣ ከአማራና ከኦሮሚያ ክልሎች ከዞኖች ጋር አቻ ከሆኑት የባህር ዳር፣ የደሴ፣ የጎንደር፣ የአዳማና የጅማ ከተሞችን፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ የካማሼ ዞንን፣ የጋምቤላ የሁሉንም ዞኖችን፣ እንዲሁም ከራሱ ከደቡብ ክልል ደግሞ የሸካ ዞንን በሕዝብ ብዛት ይበልጣል፡፡ የጋምቤላ ክልል ከኮንሶ ሕዝብ ወደ 80 ሺሕ በሚጠጋ ቁጥር ብቻ ነው የሚበልጠው፡፡

ራስን በራስ የማስተዳደር መብት

የኢፌዴሪ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 89(1)፣ መንግሥት በዴሞክራሲያዊ መርሆች ላይ በመመሥረት ሕዝቡ በሁሉም ደረጃዎች ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን ሁኔታ ማመቻቸት ያለበትን ስለመሆኑ የፖለቲካዊ ፖሊሲው በጥቅሉ አስቀምጦታል፡፡ ማንኛውም የብሔርነት፣ የብሔረሰብነት ወይንም ደግሞ የሕዝብነት ዕውቅና ያገኘ ማኅበረሰብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱን ተግባራዊ የሚያደርግበትን አስተዳደራዊ መዋቅር የመመሥረት ገደብ የሌለው ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳለው የፌዴራሉም የክልሎችም ሕገ መንግሥት አንቀጽ 39 (3) ላይ ተደንግጓል፡፡ ራስን የማስተዳደር ሙሉ መብት በክልል ላይ ብቻ የተንጠለጠለ አይደለም፡፡ ይህ መብት ውጤታማ እንዲሆን ያልተማከለ አስተዳደር ተግባራዊ መሆን አለበት፡፡ ያልተማከለ አስተዳደርን እንደ አንድ ፕሮግራም ብናየው ብዙ የሚያካትታቸው ነጥቦች አሉት፡፡ ከሚያካትታቸው ነጥቦች ውስጥ በባህርያቸው የአካባቢው መንግሥት ሥልጣንና ሥራ የሆኑትን ለአካባቢው መተው፣ እንዲሁም ባህርያቸው አካባቢያዊ ባይሆኑም እንኳን እነሱ ቢፈጽሟቸው የሚሻል ከሆነም ለአካባቢው መንግሥት መተው አለባቸው፡፡ እንዲህ መሆኑ ከታመነበት ግጭትን ለመቀነስም ሆነ በልበ ሙሉነት ለመሥራት ሲባል ሥልጣንና ተግባራቸው በግልጽ ተለይቶ መቀመጥን ይፈልጋል፡፡

የአካባቢ መንግሥታት (Local Government) የራሳቸውን ጉዳይ በራሳቸው የመጨረስ፣ ፖሊሲ የመንደፍ፣ ለፖሊሲያቸው የሕግ ማዕቀፍ የመስጠት የመጨረሻ የሥልጣን ባልተቤት መሆን ያሻቸዋል፡፡ አካባቢያዊ መንግሥታት አስተዳደራዊ ተቋሞችን የማቋቋምና ለሥራ ምቹ በሚሆን መንገድ በነፃነት የማዋቀርና የሰው ኃይል የመቅጠርም የማባረርም ሥልጣንን ይይዛል፡፡ ስለሆነም አካባቢያዊ መንግሥታት ፖለቲካዊ፣ የገቢና ወጪ፣ እንዲሁም አስተዳደራዊ ሥልጣንን ያካትታል ማለት ነው፡፡ ይህ አሠራር የማዕከላዊ መንግሥት ድጋፍና ቁጥጥር እንዲሁም በይነ መንግሥታዊ ትብብርንም አያስቀርም፡፡

ፖለቲካዊ ራስ ገዝነት ባልተማከለ አስተዳደርም ይሁን ራስን በራስ በሚያስተዳድሩ ብሔሮች ዘንድ ቁልፍ የሆነ ጉዳይ ነው፡፡ ማዕከላዊም ይሁን የክልል መንግሥታት  ባሰኛቸው ጊዜ የሚያፈርሷቸው ሲመቻቸው ደግሞ የሚያቋቁሟቸው ልዩ ዞኖች፣ ወረዳዎች፣ ቀበሌዎች ሊኖሩ አይገባም፡፡ ቀጣይ መሆን አለባቸው፡፡ በመኖርና በመፍረስ በሥጋት እየወላወሉ የሚኖሩ ተቋማት ሊሆኑ አይገባቸውም፡፡ ወይንም ደግሞ እንዴት እንደሚቋቋሙም ይሁን እንደሚፈርሱ ግልጽ ሕግ፣ ሁሉም የተስማሙበት ኖሮ በዚያው መሠረት መፈጸም አለበት፡፡ የኮንሶ ነገርም፣ በአንድ ወቅት ልዩ ዞን የነበረች ሲሆን፣ አሁን ግን መደበኛ ወረዳ ብቻ በመሆን በሰገን ሕዝቦች ሥር ትገኛለች፡፡

በሕገ መንግሥቱ በአንቀጽ 50(4) ከተገለጸው አንፃር ቋሚነት አላቸው ማለት ቢቻልም በተግባር እንደታየው ግን፣ ከ1994 ዓ.ም. በፊት ይህ ዓይነት ሥልጣን የሌላቸው ሲሆን፣ በኋላ ደግሞ መለወጡ ብሎም በአንዳንድ ክልሎች ሥልጣናቸው በሕገ መንግሥት ሳይሆን በአዋጅ መገለጹ ወይንም በግልጽ አለመቀመጡ አጠራጣሪ አስመስሎታል፡፡ በተጨማሪም እንዴት ወረዳዎች እንደሚመሠረቱና እንደሚታጠፉ፣ ድንበራቸው እንደሚካለልና እንደሚለካ አለመገለጹ፤ መሥፈርቶቹን አንዳንድ ክልሎች በአዋጅ (ለምሳሌ ደቡብና ኦሮሚያ) ሌሎቹ ደግሞ ለአስፈጻሚው አካል መተው (ለምሳሌ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና አማራ) ጉራ ማይሌ አድርገውታል፡፡ በመሆኑም ለልዩ ዞኖችም ይሁን ወረዳዎች የተሻለ ዋስትና መስጠት ያስፈልጋል፡፡ የዚህ ዋስትና አለመኖር ነው ኮንሶን በአንድ ወቅት ልዩ ወረዳ፣ በሌላ ጊዜ መደበኛ ወረዳ በመሆን ምናልባትም ለተለያዩ ተቃውሞዎች መነሻ የሆነው፡፡

የልዩ ዞንና ወረዳ ምሥረታ ሒደት

በሽግግሩ ዘመን ሥራ ላይ በነበረው አዋጅ ቁጥር 7/1984 መሠረት ወረዳን ጨምሮ ወደ ላይ ያሉ መስተዳድሮችን ማቋቋም የማይችሉት በግልጽ ተዘርዝረው ነበር፡፡ በሕገ መንግሥቱ ይህ ገደብ ተነስቷል፡፡ በተጨማሪም ክልል መመሥረት እንደመገንጠል ሁሉ ገደብ የለውም፡፡ ለነገሩ ክልል መመሥረትም ጉዳዩ ከክልል መሆኑ ነው እንጂ ያው መገንጠል ነው፡፡ ገደብ አለመኖሩን ለማመልከት ‹‹በማናቸውም ጊዜ›› የሚል ቃል ተጠቅሟል፡፡ በሕገ መንግሥቱ እንዲህ ዓይነቱ ‹‹መድልኦ›› ተወግዷል ብንልም እንኳን  በጋምቤላ አኙዋ፣ ኑዌርና መዠንግር ልዩ ዞን ሊያቋቁሙ እንደሚችሉ ሲገለጽ ኡፖና ኮሞ አይችሉም በማለት የክልሉ ሕገ መንግሥት ገልጿል፡፡ በዚህም ከብሔረሰቦች መርጦ ለዞንና ለወረዳ አለ ማለት ነው፡፡ ቁጥራቸው አናሳ (በ1999ኙ ዓ.ም. በተደረገው ቆጠራ በክልሉ ውስጥ የሚኖሩት ማኦ 64፣ ኡፖ ደግሞ 990) መሆናቸው አንድ ነገር ሆኖ በሕገ መንግሥት መከልከል ደግሞ ሌላ ነገር ነው፡፡

የአሁኑ ደቡብ ክልል ከመመሥረቱ በፊት አራት ክልሎች ነበሩ፡፡ አንድ ክልል ከሆኑ በኋላ ዞኖችና ወረዳዎች በተለያዩ ጊዜያት እንደገና ተዋቅረዋል፡፡ ለምሳሌ ሰሜን ኦሞ (ወላይታ፣ ጋሞ ጎፋ፣ ዳውሮ) ወደ ሦስት ብሔረሰብ ዞኖች ተከፋፈለ (ወላይታ፣ ጋሞ ጎፋና ዳውሮ) ተብለው፡፡ እንዲሁም ሁለት ልዩ ወረዳዎች ተጨመሩ ባስኬቶና ኮንታ፡፡ ሌላ ካፋ ሸካ የሚል እንደ አንድ ልዩ ዞን  ቢቋቋሙም ውሎ አድሮ ካፋና ሸካ ልዩ ዞኖች ተብለው ራሳቸውን ቻሉ፡፡ ቤንችና ማጂ ይባሉ የነበሩት ሁለት ዞኖች፣ ኋላ ላይ ቤንች ማጂ ተብለው አንድ ዞን ሆኑ፡፡ ስልጤ ዞንም ከጉራጌ ተነጥሎ ራሱን ቻለ፡፡ ቀደም ሲል ስምንት ልዩ ወረዳዎች የነበሩ ሲሆን፣ አሁን አራቱ (ኮንሶ፣ ደራሼ፣ ቡርጂና አማሮ) በአንድነት ሰገን ዞንን መሥርተዋል፡፡

ቋንቋ፣ ማንነት፣ የአሰፋፈር ሁኔታና ፍቃደኝነት ላይ መሠረት በማድረግ የሚቋቋሙ አካባቢያዊ መስተዳድሮች (Local territorial autonomy) ጉዳትም እንዳላቸው የሚገልጹ አሉ፡፡ ከእነዚህም ጉዳቶች መካከል ክፍፍልን ያባብሳል፣ ክልሎች በአብዛኛው ወጥ የሆነ አንድ ብሔር ስለማይኖርባቸው አሁንም ቢሆን በኢትዮጵያ የአናሳና የብዙኃንን ግንኙነት ማስቆም አያስችልም፡፡ በተጨማሪም አሁን ባለው ሁኔታ ዞኖችና ወረዳዎች ሲዋቀሩም ይሁን ሲዋሃዱ ወጥ የሆነ የታወቀ ሕገ መንግሥታዊ መርሕ የለውም፡፡ እንደ ገዥው ፓርቲ የፖለቲካ ግምገማና ድምዳሜ የሚወሰንና ዘፈቀዳዊም ነው የሚሉ ክሶች ይቀርባሉ፡፡

የዞንና ምሥረታ በደቡብ

ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ማንነታቸው ከታወቀ እንደቡድን ማንኛውንም አስተዳደራዊ እርከን የመመሥረት መብት አላቸው ብለናል፡፡ ከደቡብ ውጭ ያሉት ክልሎች፣ በውስጣቸው የሚገኙት ነባር ብሔረሰቦች ቁጥራቸው ዝቅተኛ ስለሆነ፣ ወይ መሥርተዋል፤ አልያም ትተዋቸዋል፡፡ መመሥረት ቢፈልጉ ደግሞ እንዴት ጥያቄያቸውን እንደሚያቀርቡ፣ ለማን እንደሚያቀርቡ፣ ምን ምን ሁኔታዎችን ማሟላት እንዳለባቸው ወዘተ. የሚያሳይ ሕግ የላቸውም፡፡ ደቡብ ግን አለው፡፡ የደቡብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት ስላለው፣ የዞንም ይሁን የወረዳ አመሠራረት ጥያቄ እንዴት መስተናገድ እንዳለበት፣ ይህንን ምክር ቤት ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመወሰን በወጣው አዋጅ ላይ ተገልጿል፡፡ ሥነ ሥርዓቱ ከክልል ምሥረታ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ልዩነቱ ጥያቄውን ያቀረበው በአስተዳደራዊ መዋቅር ተደግፎ ከሆነ (ለምሳሌ ልዩ ወረዳ የነበረው ልዩ ዞን መሆን ቢፈልግና ጥያቄው የቀረበው የወረዳው መስተዳደር ቢሆን) የመስተዳድሩ ምክር ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ከደገፈው ወይንም ጥያቄውን ያቀረበው፤ ሕዝቡ ከሆነ (5 በመቶ የሚሆነው ስምና ፊርማ አስፍሮ) ሕዝቡ በአብላጫ ድምፅ ሲደግፈውና የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ሲወስን ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

በዚህ ሕግ መሠረት ሕዝቡ በአብላጫ ድምፅ ወስኖ እንኳን ምክር ቤቱ ተጨማሪ ማስረጃ የማሰባሰብ ሥልጣን ስላለው አሰባስቦ ከመረመረ በኋላ ነው ውሳኔውን የሚያሳውቀው፡፡ ውሳኔውን ያሳውቃል ማለት ሕዝቡ በአብላጫ ድምፅ የወሰነውንም ሊሽረው ይችላል ማለት ነው፡፡ ይህ ዓይነቱ አሠራር ወለፈንድ ይመስላል፡፡ ድምፅ ሳይሰጡ ቢሆን እንኳን ይሻላል፤ ድምፅ ሰጥተው ከጨረሱ በኋላ የሌሎች ብሔረሰቦች ተወካዮች የሕዝብን ውሳኔ ካላከበሩ የት ላይ ነው ታዲያ የራስን ዕድል በራስ መወሰኑ? ይሄው ሕግ ይሄንኑ ጉዳይ በሚደነግግበት ክፍሉ ስለየራስን ዕድል በራስ መወሰን ነው የሚያወራው፡፡ በራሳቸው የወሰኑት ከተሻረ የትኛው ዕድላቸው ላይ ወሰኑ? ሌላው ይህ ሕግ በዝርዝር ባያብራራውም በውሳኔው መሠረት ለብቻቸው ተለይተው ራሳቸውን ማስተዳደር የሚጀምሩት ብሔረሰቦች ቀድሞ ከነበሩበት ዞን ወይንም ወረዳ ፍትሐዊ የሆነ የሀብት ክፍፍል ሊያደርጉ እንደሚችሉ አስቀምጧል፡፡ ክልል ሲመሠርቱ ያልተቀመጠውን፣ በደቡብ ክልል ውስጥ ዞንና ወረዳ (ልዩም ይሁን አይሁን) ሲመሠርቱ የንብረት ክፍፍል እንዲደረግ ያስቀምጥና ስለተግባራዊነቱም የብሔረሰቦች ምክር ቤት እንደሚከታተል ገልጿል፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አዋጅ ወይንም የፌዴራሉ ሕገ መንግሥት ስለ ክልል ምሥረታ ያላስቀመጠውን በሥሩ ለሚገኙ መስተዳድሮች ማስቀመጡ ለፌዴራሉም መንግሥት ትምህርት ነው፡፡

የክልሉ ብሔረሰቦችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች ሚና ሲገመገም

ከላይ በጥቅሉ ባስቀመጥነው መሠረት የኮንሶን ጉዳይ እንመልከተው፡፡ የኮንሶ ሕዝብ ከጠቅላላው አምስት በመቶ ድጋፍ ካገኘ በክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት አማካይነት ሕዝበ ውሳኔ ይካሄዳል፡፡ የልዩ ዞንነቱን ጥያቄ አብዛኛው ድምፅ ሰጪ ከደገፈው ውጤቱ ለክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ የዞን ምሥረታው ተግባራዊ ይሆናል፡፡ ምክር ቤቱ፣ ስለ ድምፅ አሰጣጡና በአጠቃላይ ስለ ነበረው ሁኔታና ሒደት ካጣራ በኋላ ሊያፀድቅም፣ ሊሽረውም ይችላል፡፡ ጥያቄው አዲስ ክልል የመመሥረት ቢሆን ኖሮ ግን፣ ጥያቄውን ያቀረበው ብሔረሰብ ምክር ቤት፣ ለምሳሌ ሲዳማ ቢሆን የሲዳማ ምክር ቤት፣ በሁለት ሦስተኛ ድምፅ ድጋፍ ካገኘ ይሄንኑ ውሳኔ በጽሑፍ ለክልል ምክር ቤት ያቀርባል፡፡ ጥያቄው የቀረበለት የክልል ምክር ቤት ሕዝበ ውሳኔ ከማዘጋጀት የዘለለ በሕግ የተቀመጠ የመከልከል ወይንም ሌላ ሥልጣን የለውም፡፡ ጥያቄውን ለማብረድ ፖለቲካዊ ሥራ ሊሠራ ይችል ይሆናል፡፡ ጥያቄው በደረሰው በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ድምፀ ውሳኔ ማዘጋጀት አለበት፡፡

የኮንሶን በተመለከተ፣ የደቡብ ክልል የብሔረሰቦች ምክር ቤት አንድም ሙሉ በሙሉ ጥያቄውን ካልተቀበለ አሊያም ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ ካላዘጋጀ ወይንም ደግሞ የሕዝበ ውሳኔውን ውጤት ከሻረው ጉዳዩን በይግባኝ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ማምጣት ይቻላል፡፡ ምክር ቤቱ ጥያቄውን በአዎንታ ተቀብሎ ሕዝበ ውሳኔ ሊያዘጋጅ መሆኑን የሚያሳዩ መረጃዎች መኖራቸውን ስለማይታወቅ ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት ሊመጣ ይችላል ማለት ነው፡፡ የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት አወቃቀሩ ልክ እንደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ ውስጥ የሚገኙ ከእያንዳንዱ ብሔር አንድ አባል ያለበት፣ ነገር ግን ከአንድ ሚሊዮን በላይ ቁጥር ካለው ለእያንዳንዱ አንድ ሚሊዮን ሌላ ተጨማሪ አንድ አባል ለምክር ቤቱ ይጨመርለታል፡፡ አባላቱ የሚመረጡት የብሔረሰቡ ዞኖች ወይንም ወረዳዎች ምክር ቤት መካከል ሆኖ መስተዳድር ከሌላቸው ግን በቀጥታ ከብሔረሰቡ ተመርጠው ይወከሉበታል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ደግሞ ለክልል ምክር ቤት ከተመረጡ ተወካዮች ውስጥ በክልሉ አሸናፊ የሆነው የፖለቲካ ፓርቲ የፈለገውን ሰው ከምክር ቤቱ አባላት መርጦ ይልካል፡፡ ስለሆነም፣ የደቡብ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት የሚኖረው የአባላት ብዛትና ክልሉ በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚኖረው ውክልና እኩል ነው፡፡

የኮንሶ ብሔረሰብ፣ ቢያንስ 65 አባላት በሚኖሩት የብሔረሰቦች ምክር ቤት አንድ ወኪል ይኖረዋል፡፡ በፌዴሬሽን ምክር ቤትም እንዲሁ፡፡ ከሕገ መንግሥታዊነትና ሕጋዊነት ይልቅ፣ ከሕገ መንግሥቱ ጋር አብሮ በማይሄደው ፓርቲያዊ የሆነው ዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት ላይ በመመርኮዝ ውሳኔዎች እንደሚሰጡ ስለሚታወቅ፣ የብሔረሰቦቹ ምክር ቤት አባላትም ለተመረጡበት ፓርቲ መታመን ስለሚጠበቅባቸው በክልልና በፌዴሬሽን ምክር ቤቶች መካከል የተለያዩ ውሳኔዎችን መጠበቅ አይቻልም፡፡ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች በክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት ላይ የሚኖራቸው ተፅዕኖ በቀላሉ የሚታይ አይደለም፡፡ የበለጠ የሚከፋው ደግሞ እነዚህ የክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የክልሎቹን ርዕሰ መስተዳደር ጨምሮ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባል መሆናቸው ነው፡፡ ክልል ላይ ላደረሱት በደል አቤቱታ ሲቀርብባቸው፣ በፌዴሬሽን ምክር ቤት በዳኝነት ይሰየማሉ፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ካሉት 153 አባላት ውስጥ፣ ከ65 የማያንሱ ከደቡብ ክልል የተወከሉ ናቸው፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች የክልሉ አቋም ለኮንሶ የዞን ጥያቄን አለመቀበል ከሆነ፣ የፓርቲውን ጫናና የተማከለ ውሳኔውን እንኳን ብንተወው፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ላይ አብላጫ ድምፅ ለማግኘት በጣት የሚቆጠሩ ደጋፊዎችን ማፍራት ብቻ ነው የሚጠበቅበት፡፡

የኮንሶ ብሔረሰብ ወደ ኦሮሚያ ክልል ለመጠቃለል

የፌዴራሉ ሕገ መንግሥት እንዴት መገንጠል እንደሚቻል እንጂ ሌሎች አገሮች ከኢትዮጵያ ጋር መዋሃድ ቢፈልጉ እንዴት ሊቀላቀሉ እንደሚችሉ የሚገልጽ ሥነ ሥርዓት አላስቀመጠም፡፡ አንድ ክልል ከሌላ ክልል ጋር መዋሃድ ቢፈልግ ወይንም አንድ ብሔር ከአንድ ክልል ወጥቶ ወደ ሌላ ክልል መካለል ቢፈልግ፣ ይሄንን ማስተናገድ የሚችል ግልጽ የሆነ ሕግ የለንም፡፡ እንደ አዲስ ክልል መመሥረት ለሚፈልግ ሥርዓት አለው፡፡ ግንኙነቱም በተገንጣዩና በቀሪው ክልል መካከል ይሆናል፡፡ ወደ ሌላ ክልል መጠቃለል ከሆነ ግን የሌላ ክልል ተሳትፎን ይጠይቃል፡፡

የኮንሶ ሕዝብ በኦሮሚያ ክልል ከቦረና፣ ሊበን ከሚባለው አካባቢ መጣን ብለው ስለሚያምኑ፣ የቋንቋው ቤተሰብም ኩሽቲክ በመሆኑ፣ ከኦሮሞ ሕዝብ ባህል ጋር የሚመሳሰሉ ልምዶች ስላላቸው ይመስላል ይህ ዓይነት አማራጭ ሊነሳ የቻለው፡፡ የሁለቱ ክልሎች ቅንነት እስካለ ድረስ የድንበር ግጭት ሊፈታ በሚችልበት መንገድ በስምምነት መጨረስ ይቻላል፡፡ በተጨማሪም፣ የድንበር ማካለል ጥያቄ በማንሳት በሕዝበ ውሳኔ መፍታት ይቻላል፡፡ ይህን ለማድረግ ግን፣ በኮንሶ ጉዳይ፣ የኦሮሚያ ክልል የድንበር ጥያቄ ማንሳት ወይንም የሕዝቡን ጥያቄ መቀበል አለበት፡፡ ከወልቃይት ጉዳይ የሚለየው የኮንሶ ሕዝብ የኦሮሞነት ጥያቄ አለማንሳቱ ነው፡፡ ሁለቱም ቢሆኑ የድንበር ማካለል ብቻ አይደሉም፡፡ እንደዚህ ዓይነት ጥያቄዎችም ሕጋዊ አሠራር የሚያስፈልጋቸው ይመስላል፡፡

ሲጠቃለል፣ ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በማናቸውም ጊዜ ክልል የመመሥረት ሕገ መንግሥታዊ የሆነ መብት አላቸው፡፡ ነገር ግን ከሰማንያ በላይ ክልል የማቋቋም አቅም አለን ወይ? እንኳን ክልልና ወረዳና ዞን መቋቋምም ከወጪ አንፃር ከባድ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት ብሔረሰቦች ቁጥራቸው ከ100,000 በታች ሲሆኑ፣ ሃያ አንዱ ደግሞ ከ10,000 በታች ናቸው፡፡ ለቀበሌና ለወረዳ የመሳሰሉት አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትንስ መቋቋም ይቻላልን? የበጀት፣ የሰው ኃይልና የመሳሰሉትን ፍላጎቶች መሸፈን መቻሉ አጠራጣሪ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መተግበር የማይቻል መብት ውሎ አድሮ ቅያሜ ማምጣቱ አይቀርም፡፡ የኮንሶም ጉዳይ ይኼው ነው፡፡ እናም የአሰፋ አባተን ግጥም ልዋስና ልደምደም፡፡

‹‹የማትበላ ወፍ ተይዛ በጭራ፣

ልቤን አደማችው ሞጭራ ሞጫጭራ፤››

እንዳለው የማይተገበር መብት አስቀምጦ የሰው ሕይወትና ንብረት እንዲጠፋ ምክንያት ከመሆን እንደ አዋጅ ቁጥር 7/1984 በግልጽ የትኞቹ ብሔረሰቦች ምን ዓይነት መስተዳደር ማቋቋም እንደሚችሉ አስቀድሞ ሕገ መንግሥቱን በማሻሻል ማስቀመጥ፣ ወይንም ደግሞ መብቶቹን ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡ አንድ ጊዜ ልዩ ወረዳ፣ ሌላ ጊዜ እንደ ኮንሶ፣ ከሌሎች ጋር በመቀላቀል ዞን ማድረግ ግጭትን መጥራት ነው፡፡ ተመጣጣኝ የሕዝብ ቁጥር እያላቸው፣ አንዱን መርጦ ዞን እንዲኖረው ማድረግ ፍትሐዊ አይደለም፡፡

አዘጋጁ፡– ጸሐፊውን በኢሜይል አድራሻቸው wuobishett@yahoo.com ማግኘት ይቻላል፡፡

የኮንሶ ጥያቄ ግጭት እና መፍትሄው ውይይት በዶቸ ቨሌ

የድምፅ መረጃን ያዳምጡ Click below

http://dw.com/p/1K7TM

 

 

 

 

 

 

 

View Post

ወጣት ዮናስ አሰፋ /ቡቱሌ/ በልዩ ሃይል ታፍኖ ተወሰዴ

In News by Konso People1 Comment

በዛሬው እለት 21/9/2016 በግድ ስብሰባ ካልገባችሁ ብለው የካራት ከተማ ነጋዴዎችን እያስገዱና በጉልበት ለመሰብሰብ እየሞከሩ መሆኑን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ይህ በእንድህ እንዳለ በልዩ ስሙ ቡተሌ የተባለ ወጣት ነጋዴ በጠሩት ስብሰባ ላይ ባለመገኘቱ በወታደሮች ተወስዶ መታሰሩን ከ ካራት ከተማ መረጃዎች ደርሰውናል፡፡

እንዲሁም በካራት ከተማ ነጋዴዎችን በጠብመንጃ እያስፈራሩ ለመሰበሰብ ሞክረዉ አልተሳካላቸውም፡፡
በተጨማሪም በቴ/ሙያ ኮሌጅ ሲሰቃዩ የነበሩ ከ40 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎቻችንን የበለጠ ለማሠቃየት አርባምንጭ ወስደዋል፡፡

በ አሁን ጊዜ በሽህዎች የሚቆጠሩ የካራት አከባቢ ወጣቶች እስርና እንግልትን ሸሽተው በየጫካው ስደት ላይ ይገኛሉ፡፡ በኮንሶ ህዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ኢ-ሰብአዊ ድረግቶች በአስቸኳይ እንዲቆምና ያለ ምንም ክስና ወንጀል የታሰሩ የኮንሶ ወጣቶች እንዲፈቱ በአጽንኦት እንጠይቃለን፡፡

View Post

Konso Crisis በኮንሶ ሕዝብ ላይ ከባድ የሕይወት፥ የሰብአዊና የኢኮኖሚ ውድመት እየደረሰ ነው

In Image, News by Konso People3 Comments

The Konso are Cushitic people living in the southern region of Ethiopia according to the ethnic based cstr4ucture of Ethiopian government. The Konso are well known for their hardworking and terracing in the world. Their land usage and management made them known in the world being registered in UNESCO for their landscape.

They are currently passing through the valley of sorrow and destruction by Ethiopian government, particularly by southern Ethiopia government.

The following are some of the cruelty being executed up on Konso people.

Burning of Villages

See pictures of burnt Kebeles at Aylota

konsovilageburnkonsovilage-burning

The Konso are known for their unique way of settlement on hilly areas with homes made up of grass. The hatches houses are the identification of Konso people.

Recently, the government troops burned the villages in response to the people’s requisition for zonal administration. The question is in accordance to Ethiopian constitution.

 • The government bodies arranged for controlled conflict and supplied armaments for some deviant anti-people groups to burn and destroy the Konso who asked the constitutional zonal question in a village called Aba Roba, or Ayayet. The reason of burning is purposive action to gain political benefit from the government side. The Konso has been tolerant since last September of 2015 not to respond in any forceful way. Their trend was absolutely peaceful and constitutional. The government sent troops from the segen zone and consequently from the region to suppress the question of the people in force. Yet people’s response was peaceful and legitimate. So in order to provoke anger and violence they officials arranged conflict to cause division among the people, for that consumption they burned the village of Ababa Roba.
 • The government officials, arranged robbers to destroy, robe, burn and kill people in area called Aylota. They did it. Killing with modern sniper guns and at the back a group vagabonds to robe, burn villages.

 

 

 

 Killings and Injuries

The special military force, the defense force of the nation and zone police together, surrounds and kills people in villages around Karate town. They have killed a 36 years old farmer named Sagoya Chucha  in Durite village and many were injured badly and more than 70 people were incarcerated.

Below is the image of the farmer killed by the government military force. He is called Sagoya Chucha was killed by the military forces in Durite Kebele of Konso

14358635_631304983697179_7153064262188835953_n

14432983_1660764710902712_3644778357649496961_n

 

This young boy is called Temesgen Tesfaye. The military forces have shot him and his hand is completely destroyed.

14440637_631304907030520_7592883708208547931_n

 

His name is Berisha Orkaido (Banchulo), a teacher in profession: they shot him on his leg and bitten him cruelly. He is between life and death

14440684_307758646274199_2685268418987146079_n

 • The government officials and the military forces are persecuting the coordinating committee of the constitutional questions. The 23 coordinating committee for the zonal administration are currently persecuted to kill or arrest. They were selected from all segment of the people, religious, business men, scholars, farmers, cultural leaders and elders of the people. The selection was made officially by Police officer who came from Federal government at a place called Pasqa, Kamole. But today by the government media they are labeled as terrorists.
 • All service centers are closed: Government offices, shops, clinics and health centers

በኮንሶ  ሕዝብ  ላይ ከባድ  የሕይወት፥  የሰብአዊና የኢኮኖሚ  ውድመት እያደረሰ  ነው

የኮንሶ ህዝብ በዞን የመደራጀት ጥያቄውን በሰላማዊና በሕገመንግስታዊ መንገድ ካቀረበበት ካለፈው ዓመት ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ በኮንሶ ሕዝብ ላይ እየደረሰ ያለው ውድመትና ስብኣዊ ድርጊቶች  “ከማጥ ወድ ዲጥ”  እየሄደ ይገኛል።

በተለይም ባሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ መከላከያ ጦር፥ የደቡብ ክልል ልዩ እና  በሰገን አካባቢ ሕዝቦች ኃይል በንፁህ የኮንሶ ሕዝብ ላይ እየተወሰዱ ያለው መጠነሰፊና ዘግናኝ ጦርነት እስከ ዛሬ ድረስ  በከፋ ሁኔታ  ቀጥሎአል።

በተለይም ካለው ዓመት  ከጳጉሜ 5 ቀን 2008 /  አባ ሮባ በሚባል ቀበሌ ገበሬ ማህበር መንደራት በመንግስት እካላት የተቀነባበረ ቃጠሎን ተከቶሎ የዞኑ መቀምጫ ወደ ሆነችው ወደ ጎማይዴ አካባቢ ተዛምቶ ወደ ለየለት የመንግስት መካላከያና የክልሉ ልዩ ሐይል ጦርነት ተቀይሮ ይህ ነው የማይባል አካላዊና፥ ሞራላዊና ኢኮኖሚያዊ ውድመትናና እልቅትን እያስከተለ ይገኛል።

ከጉማይዴ የሺ ቤቶች ቃጠሎና የብዙ የሕዝብ እልቅት በኋላ፥ ጦሩ እቅጣጭውን የቆየ የክልሉ ልይዩ ሀይልና ሎችች ታጣቂ ሀይሎቾ በሚያስትጨንቁት ወደ ዋና የኮንስ ምድር በማምራት እስክ  መስከረም 9 2017 ዓም ከፍትኛ ውደመትና የጅምላ እስራት በማካሄድ ላይ ይገኛል።

ባሁኑ ሰዓት ጦርነትና ልዩ አፈና እየተካሔደበት ያለው ከብዙ ዘምናት ቆይታ በኃላ በዩኒስኮ ከተመዘገቡትና ሕዝቡ በተፈጥሮ ልዩ ጥብቃና እንደ አይን ብሌኑ በሚንከባክከክባቸው መንድሮች መካከል በዶካቱ፥ በፐንከልቶ ግድያና የጅምላ አፈናና እስራት በማካሔድ፥ ከዚያም አልፎ በመላውን የኮንሶ መደራት ላይ መጠነሰፊ ድብደባ፥ እስራት፥ግድያ የጦር ነክ ውንጅሎች  ስልታዊ  በሆን መልክ እየተካሄደ ይገኛል፥ 

ለምሳሌ ያህል በመስከረም 9 2009 ዓም ጥዋት በማልዳ መከላከያ ጦር ወደ የፐታንካልቶን መንደሩ ዙርይያውን ከብቦ ወድ መንድሩ በሙሉ የጦር ትጥቅ በመግባት፥ በመንድሩ ንፁህ ነዋሪዎች ማለትም ሕፃናት፥ ሴቶች አረጋዊያን ላይ ከፍተኛ የትኩስ እሩምታ በማዝነብ እስከ አሁን ድረስ ሁለት ሰዎች በይፋ መሞታቸው ሲታወቅ፥ ሌሎች ብዙ ሰዎች በሞትና በህይወት ጣር ላይ ናቸው።

ይህ እንዲህ እንዳለ፥ ባሁኑ ሰዓት በኮንሶ ሕዝብ ላይ መከላከያ ጦርና የክልሉ ልዩ ሀይል እንዲሁም ልሎች ሀይሎች እያደረሱት ያለው ሰብዓዊ፥ ኢኮኖሚያዊና የህይወት እልቅት የኮንሶ ሕዝብ በታሪኩ ሰምቶትና አይቶውት የማያውቅ ጦርነት እያስተናገደ ይገኛል። ከዚህም እሳዛኝ ጦርነት የተነሳ፥ ባሁኑ ሰዓት፥ ከህፃናትና መንቀሳቀስ ከማይችሉ አረጋዊያን በስተቀር፥ ሰዎች አገር ለቅቀው እየጠፋ፥ አካባቢው ጭው ጭር፥ ፀጥ፥ ረጭ ብሎእል። 

 ስለዚህ ይህ በሰላማዊ ሕዝብ ላይ የተከፈተው የሀገር ውስጥ ጦርነት፥ ድብደባ እስራት የአካል መጉዳት ዝርፊያና ሌሎች ስልታዊ ጦርነክ ወንጀሎች በጊዜ፥ ቆሞ የሀገር መከላከያ ጦርና የክልሉ ልዩ ሀይል፥ ከምድርቱ ፍፁም ለቀቆ ካልወጣ፥ የኮንሶ ህዝብን ከአከባቢ ሁሉ ሊያጥፍ  እንድሚችል የእካባቢው አባቶችና ነዋሪዎች ከፍተኛ ስጋት አላቸው።  ይህ እየተካሄዴው ያለው በጦርነትና ውድመት በእስቸካይ  ካልቆመ የኮንሶ ሕዝብ ለሚቀጥሉት ዘመናት በፍፁም የማይረሳው ጥቁር ታሪክን በህዝቡ ስነልቦና ላይ ፅፎ እያለፈ ይገኛል። 

በመሆኑም ማንኛውም ኢትዮጵያዊም ሆነ ሰብአዊ ሰውና ህልና ያለው ሰው ታታሪውና ሰላማዊ የሆነውን የኮንሶ ሕዝብን ለረጅም ጊዜ እያስጨነቀና እያጠፋ ያለውን ሰብአዊ ድርጊት፥ ድብደባና ግድያና የጅምላ እስራት በአፋጥኝ እንዲቆም ባላችሁበት ስፍራና ጊዜ ድምፃችሁን እንድታሰሙና እንድትድርሱለት የይድረስ ጩሔቱን ጥሪውን ያቀርባል፡፡

 

 

View Post

Fundraising for displaced People of Konso ለኮንሶ ተፈናቃዮች የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ !

In Link by Konso People2 Comments

We the, concerned individuals of Konso, residing outside Ethiopia are appealing to the international community, individuals, organizations and right groups for humanitarian assistance for the over 25, 000 internally displaced people (IDP) of Konso in Southern Ethiopia.  Just last week alone, around 50 civilians were killed and over 100 people were unaccounted for. Over 25,000 people were displaced when their villages recognized by the United Nations Educational, Scientific and Cultural Organization (UNESCO) in 2009 were burned to the ground (see attached pictures).  This number is expected to grow because regime forces are still shooting at unarmed civilians and burning villages.
Dead bodies from last week’s killings are still lying on the ground with morgues decomposing in torched villages and homesteads because regime forces would not allow people to collect and bury their loved ones. As we speak today, a battalion of regime forces (over 600 well-armed troops) have been rounding up people from villages of Konso settlements in their door to door operation. Hospitals and other social service institutions have been closed over a year now with the number of death due to lack of medical attention rising each day including pregnant woman who died giving birth.
We appeal to you to help us in any way possible for the displaced and needy in Konso.

In next two days we will set up fundraising platform and open discussion forums on how to reach out to the victims, we will also contact and work with Konso Development Association (KDA) to deliver the collected help and support to victims.

konsovilage%e1%89%83%e1%8c%a0%e1%88%8eburnkonso

ለኮንሶ ተፈናቃዮች የገቢ ማሰባሰቢያ ጥሪ !

በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የዜና አውታሮችና ሶሻል ሚዲያዎች እንዳያችሁት በኮንሶ የሠፈረው የደቡብ ልዩ ሀይል እና የሀገር መከላከያ ሠራዊት ባደረሰው ጥቃትና ግጭት ከ25000 በላይ የሚሆኑ የኮንሶ አባወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ክልሎች ና በሃይማኖት ተቋማት ግቢዎች ውስጥ እንዲሁም ወደ ተለያዩ የኮንሶ ቀበለያት በመሰደድ በጥገኝነት እየኖሩ ይገኛሉ፡፡ በአሁን ሰዓት በከፍተኛ ሁኔታ የወገን እረዳታን ይሻሉ፡

ስለሆነም በመላው ዓለም የሚትገኙ የኮንሶ ተወላጆች እንዲሁም ውድ ኢትዮጵያዊያን ፤

በሀገር ውስጥ(ኢትዮጵያ) ላላችሁ

 • በኮንሶ ምሁራን(የዩኒቨረሲቲ መምህራን) አማካኝነት ኮሚቴ በፍጥነት ተቋቁሞ እርዳታዉን እንድያስተባብሩና ከኮንሶ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር እረዳታዉን ለተፈናቃዩ ህዝብ እንዲደርስ ይደረጋል፡፡

በውጪ ሀገር ለሚትገኙ

 • የገቢ ማሰባሰቢያ በኢንተርነት ተከፍቶ በማንኛውም ሰዓት እርዳታቸሁን መለገስ የምትችሉበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡

በተጨማሪ የተለያዩ ገንቢ ተሞክሮዎችንና አስተያየቶችን ቢታጋሩን በታላቅ አክብሮት ተቀብለን ተጎጅውን የኮንሶ ህዝብ ለማገዝ እንጥራለን፡፡

For more detail click on the following news links.

View Post

የኮንሶ ነዋሪዎች በመከላከያ ሰራዊቱ ጥቃት እያለቁ ነው፡፡

In Audio by Konso People0 Comments

ከጳጉሜ 5, 2008 ዓ.ም. ምሽት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ የመከላከያ ሰራዊት ኮንሶ በሚገኙ የተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪዎች ላይ ጥቃት ፍጽመዋል ሲሉ አንድ የሕዝብ ተወካይ ነኝ ያሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስታወቁ።

በጥቃቱ አያሌ ቤቶች መቃጠላቸውን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውንና ብዙ ሰዎችም የት እንደደረሱ እንዳልታወቀ ገልጸዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት ቃል አቀባይ ወ/ት ሂክማ ከይረዲን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለመስጠት ቃል ቢገቡም በስብሰባ ምክንያት ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኙ አልቻሉም።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

View Post

የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በኮንሶ መዘጋታቸውን የክልሉ መንግሥት አመነ

In News by Konso People1 Comment

በኮንሶ ከልዩ ወረዳነት ወደ ሰገን ዞን መጠቃለላቸውን የተቃወሙ የመንግሥት ሠራተኞችና የህብረተሰቡ ወኪሎች የመንግሥት ሥራ ያቆሙትና ደመወዝም አልቀበልም ያሉት በራሳቸው ፍላጎት እንደሆነ የደቡብ ክልላዊ መንግሥት አስታወቀ።

ነዋሪዎችና ወኪሎቻቸው ከ50 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላትን አዋቅረው፣ ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ፤ እስካሁን ተገቢውን ምላሽ አለማግኘቱና ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው ለዝግጅት ክፍላችን ገልጸዋል።

በኮንሶ የመንግሥት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት እንደማይሰጡ፣ ጤና ጣቢያዎችም ጭምር መዘጋታቸውን ለደሃ ደሃ የሚሰጠው የምግብ ዋስትና መቋረጡን ጭምር ይገልፃሉ።

የክልሉ መንግስት ቃል አቀባይ በበኩላቸው በዞን እንጠቃለል ለሚለው ጥያቄ ተገቢው ምላሽ መሰጠቱን ገልፀው መንግሥት መስሪያ ቤቶችን አልዘጋም፤ ጥያቄያችን ተቀባይነት ከሌለው አንሰራም ብለው የቀሩት ሠራተኞቹ ናቸው ይላሉ።

የአሜሪካ ድምፅ በጉዳዩ ላይ የሕገ-መንግስት ባለሞያንም አነጋግሯል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

View Post

የኮንሶ ነዋሪዎች መፍትሔ ማግኘት እንዳልቻሉ ተናገሩ

In Audio, News by Konso People0 Comments

ጤና ጣቢያዎች ተዘግተዋል። ለደሃ ደሃ የሚሰጥ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተቋርጧል። የመንግሥት መስሪያ ቤቶች ተዘግተዋል ብለዋል።

የኮንሶ ነዋሪዎች ከ50 ሺሕ ሰው በላይ ፊርማ አሰባስበው በሕዝብ በተመረጡ ዐሥራ ሁለት የኮሚቴ አባላትን አዋቅረው፣ ከልዩ ወረዳነት ወደ ወረዳ ወርደው በሰገን ዞን ስር እንዲጠቃለሉ መደረጋቸውን ተቃውመው፣ እንዳውም ኮንሶ ራሱን ችሎ ዞን ሊሆን ይገባዋል በሚል ያነሱት ጥያቄ፤ እስካሁን ለሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳጋለጣቸው የኮሚቴው አባል ነኝ ያሉ አቶ ገመቹ ጎንፋ ለአሜሪካ ድምፅ ተናገሩ።

ጥያቄውን ለመመለስ እና ችግሩን ለመፍታት መፍትሔ እንዲያፈላልጉ ከሕዝብ የተመረጡ 23 የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ እንደሆኑ የተናገሩት አቶ ገምቹ ገንፌ የኮንሶ ሕዝብ በአሁኑ ሰዓት ችግር ላይ መሆኑን ይናገራሉ።

ጤና ጣቢያዎች ተዘግተዋል፣ ለደሃ ደሃ የሚሰጥ የምግብ ዋስትና ፕሮግራም ተቋርጧል እንዲሁም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች መዘጋታቸውን ይናገራሉ።

ሌሎች ነዋሪዎችም ይህ ተቃውሞ ለደሃ ደሃ የሚደረገው የምግብ ዋስትና ድጋፍ እንዲቋርጥ ምክንያት እንደሆነናቸው ይገልፃሉ።

የመንግሥት ሠራተኞች ደሞዝ አልተከፈላቸውም፣ ጤና ጣቢያዎች ተዘግተዋል፣ ሰዎች በነፃነት መንቀሳቀስ አልቻሉም ሲሉ ይናገራሉ። የወረዳው አስተዳዳሪ በበኩላቸው ይህን ጥያቄ የሚያነሱት በባህል የተደራጁ ቡድኖች ናቸው ይላሉ።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

 

View Post

የኮንሶ ተወላጆች ከዩኒቨረስቲዎች እንዲባረሩ እየተደረገ ነው፡፡

In News by Konso People5 Comments

ከደቡብ ክልል ትም/ት ቢሮ የወጣው የደብዳቤ ማስረጃ እንደሚያሳየው የኮንሶ የክረምት ሥራ ላይ ስልጠና summer course የሚወስዱ የኮንሶ ተወላጆች ከዩኒቨረስቲዎች እንዲባረሩ  እና እርምጃ እንድወሰድባቸው የሚል ደብዳቤ ከታማኝ ምንጭ ደርሶናል፡ ይሄን አንድ ብሔር ላይ ያነጣጠረ እኩይ ተግባር የኮንሶ ህዘብ በአንድነት ይቃወማል፡፡
14074958_1204937102879411_832075284_o

14087591_1204939476212507_1465192206_o

View Post

የኮንሶ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፊተኛ ዉጤት አስመዘገቡ

In Image, News by Konso People1 Comment

የኮንሶ 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከፊተኛ ዉጤት አስመዘገቡ

እንደተለመደው በሠገን አከባብ ህዝቦች  ዞን ከምገኙ ወረዳዎች ትልቁ የሆነው ኮንሶ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሪከርድ በመስበር ከፊተኛ ዉጤት አስመዘገቡ::ነገሩ እንድህ ነው፡ ሰሞኑን በ south tv አልተማሩም የተባሉት የኮንሶ ተማሪዎች የተቀሩትን የ4ቱን ወረዳዎች የምያስንቅ አኩሪ የሆነ ውጤት ከብዙ በጥቂቱ እነሆ 
1.አክልሉ ኩሴ ኩርታይሌ....ውጤት 600
2.ሳሙኤል ኩስያ ቦራኖ......ውጤት 579